From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ጥንቅቅ ፡ አድርጐ ፡ ስራዬን ፡ ሰራልኝ፡ (ተፈፀመ)
እዳዬን ፡ በደሙ ፡ አወራረደልኝ ፡ (ተፈፀመ)
እውነትና ፡ ምሕረቱም ፡ ተስማሙልኝ ፡ (ተፈፀመ)
ዘላለመ ፡ በርሱ ፡ ቀን ፡ ተወሰነልኝ ፡ (ተፈፀመ)
የማረፊያ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የማረፍያ ፡ አረገው (፫x)
የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x)
እንወደው ፡ ዘንድ ፡ እንኳ ፡ ደምግባት ፡ እስኪያጣ ፡ (ተፈፀመ)
የህማም ፡ ሰው ፡ ሆነ ፡ በደዌ ፡ ተመታ ፡ (ተፈፀመ)
እንዲህ ፡ ባለመውደድ ፡ እንዲህ ፡ ባለፍቅር ፡ (ተፈፀመ)
እራሱን ፡ አሳየኝ ፡ አምኜው ፡ እንድኖር ፡ (ተፈፀመ)
የማረፊያ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የማረፍያ ፡ አረገው (፫x)
የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x)
አብ ፡ አስቀድሞ ፡ በልጁ ፡ ወሰነኝ ፡ (ተፈፀመ)
ወስኖም ፡ መረጠኝ ፡ ሊያፀድቀኝ ፡ (ተፈፀመ)
የቃሉን ፡ ብርሃን ፡ በልቤ ፡ አበራው ፡ (ተፈፀመ)
አድራሻዬን ፡ ሊያደርግ ፡ በሰማዩ ፡ ስፍራ ፡ (ተፈፀመ)
የደስታ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የደስታ ፡ አረገው (፪x)
የእፎይታ ፡ አረገው ፡ ዘላለሜን ፡ የእፎይታ ፡ አረገው (፪x)
የደም ፡ ላብ ፡ እያላበው ፡ ፍቅር ፡ ግድ ፡ ስላለው (፪x)
ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ ፡ ተፈፀመ (፪x)
|