ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው (Sew Kebur New) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፬ (14)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ማንም ፡ ወንድሙን ፡ አይናቀው (፪x)
ያገኘም ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው (፪x)
ማንም ፡ ታናሹን ፡ አይናቀው (፪x)
ያገኘም ፡ ያጣ ፡ ሰው ፡ ክቡር ፡ ነው (፪x)

ለምን ፡ ተስፋ ፡ ይቁረጥ ፡ ለምንስ ፡ ይቆዝም
ዳቦ ፡ አይሁንበት ፡ አይራበው ፡ ፍቅር

ወንድሜ ፡ መገለሉ ፡ ይቅር (፫x)

ከእናቴም ፡ ባይወለድ
የአዳም ፡ ዘር ፡ የእግዜር ፡ ፍጡር
አብሬው ፡ ልቁረስ ፡ ልስጠው
እኔ ፡ በልቼ ፡ አይራበው

አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ የራበው ፡ ሳያንሰው
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ፍቅር ፡ ሲቸግረው
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ሲያለቅስ
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ አንጀቱ ፡ ሲላወስ

መጽናናቱ ፡ (ልሁንለት )
እኔ ፡ እያለሁ ፡ (ወንድሜ ፡ አይሙት)
ትላንትና ፡ (እንዴት ፡ ይረሳል)
አፈር ፡ ባፈር ፡ (ላይ ፡ እንዴት ፡ ይኮራል)

አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ የራበው ፡ ሳያንሰው
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ፍቅር ፡ ሲቸግረው
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ ጥግ ፡ ይዞ ፡ ሲያለቅስ
አያሳዝንም ፡ ወይ ፡ አንጀቱ ፡ ሲላወስ

መፅናናቱ ፡ (ልሁንለት)
እኔ ፡ እያለሁ ፡ (ወንድሜ ፡ አይሙት)
ትላንትና ፡ (እንዴት ፡ ይረሳል)
አፈር ፡ ባፈር ፡ (ላይ ፡ እንዴት ፡ ይኮራል)

ባልንጀራህን ፡ እንደራስህን ፡ ውደድ
ለራስህ ፡ የክብር ፡ ወንበር ፡ አትውሰድ
ጌታው ፡ ሲፈርድ ፡ ኋላ ፡ እንዳትወሰድ

ባልንጀራህን ፡ እንደራስህን ፡ ውደድ
ለራስህ ፡ ክብር ፡ ወንበር ፡ አትውሰድ (፪x)