From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ንፋሱ ፡ ሲታዘዝልህ ፡ ባሕሩም ፡ ሲታዘዝልህ
አየሁት ፡ ጌትነትህን ፡ ሁሉን ፡ ማድረግ ፡ መቻልህን (፪x)
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ኦ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ልጠግብ ፡ አልቻልኩም ፡ አንተን ፡ አሞግሼ
ክበር ፡ እልሃለሁ ፡ መልሼ ፡ መላልሼ (፪x)
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ኦ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
እስከዛሬ ፡ በሕይወቴ ፡ እጅግ ፡ የተደነቅኩበት
አሰራር ፡ አደራረግህ ፡ እራሱም ፡ ያንተ ፡ ማንነት (፪x)
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ኦ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ልጠግብ ፡ አልቻልኩምና ፡ አንተን ፡ አሞግሼ
ክበር ፡ እልሃለሁ ፡ መልሼ ፡ መላልሼ (፪x)
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ኦ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ያደረክልኝ ፡ በዛ ፡ በዛ ፡ ከቁጥር ፡ በዛ
እንዲህ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ የምለውን ፡ ምላሽ ፡ እስካጣ (፪x)
ልጠግብ ፡ አልቻልኩምና ፡ አንተን ፡ አሞግሼ
ክበር ፡ እልሃለሁ ፡ መልሼ ፡ መልሼ (፪x)
ኦ ፡ ድንቅ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
ኦ ፡ ልዩ ፡ ነህ ፡ ኦ (፪x)
|