Bethlehem Tezera/Tefetseme/Meheretun Asebie

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘማሪ ቤተልሔም ተዘራ ርዕስ ምህረቱን አስቤ አልበም ተፈፀመ

ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (፫x) ዝም ብዬ ሳስብ ሳሰላስለው እግዚአብሔር እንዴት ድንቅ ነው (፫x)

አዝ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ ታዲያ እንዴት አመስግኜው ልርካ (፬x)

አልጠፋብሽ ያለኝ ከልቤ ውስጥ የእግዚአብሔርስ ፍቅር አሳዳጊነቱ አባትነቱ ከህይወቴ ጀምር ትዝታ አይደለም እያነሳሁ ምተርክለት በርሱ ይደለም ወይ እስከ አሁኗ ድረስ ያለሁት (፪x)

የእግዚአብሔር ምህረት አቤት (፫x) ሰው ወዳድነትህ አቤት (፫x) የፍቅሩ ጥልቀት አቤት (፫x) እሩህሩህነትህ አቤት አቤት አቤት (፪x)

አንድ ሁለት ብዬ ውለታውን አስቤ ልቆጥር ጥፍት ይለኛል ከየት ተነስቼ እንደምጀምር ይህ እንኳን ብረዳኝ ቢነግርልኝ ውስጤን ቢገልጸው እንደእግዚአብሔር ያለ የለም ብዬ ልደምድመው (፪x)

እንደእግዚአብሔር የለም አቤት (፫x) ቢፈለግ ዘላለም አቤት (፫x) እንደእሱ የለም አቤት (፫x) ቢፈለግ ዘላለም አቤት አቤት አቤት (፪x)

አዝ ምሕረቱን አስቤ አቤት ስል ፍቅሩ አለ ለካ ፍቅሩን አስቤ አቤት ስል ባርኮቱ አለ ለካ አለ ለካ ታዲያ እንዴት አመስግኜው ልርካ(፬x)