ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው (Gietan Maseb New) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(3)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

የሆነው ፡ ነገር ፡ እርሱ ፡ የሚሆን ፡ ነው ፡ አሃ
የተደረገው ፡ እርሱ ፡ የሚደረግ ፡ ነው ፡ አሃ (፪x)

ከፀሐይ በታች ፡ አዲስ ፡ ነገር ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ ብቻ ፡ አይለመድም (፪x)

ሰው ፡ በእውቀቱ ፡ ላይ ፡ ደርቦ ፡ እውቀትን ፡ ቢጨምር
ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ
ለዓይኑ ፡ ያማረውን ፡ ከማድረግ ፡ ነፍሱን ፡ ባይከለክል
ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ
ማረፍያዬ ፡ ብሎ ፡ ቤቶቹን ፡ ቢያሳምር ፡ ቢያስጌጥ
ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ
ብርና ፡ ወርቅን ፡ አከማችቶ ፡ ለነገው ፡ ቢያስቀምጥ
ይህም ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ከንቱ

አዝ፦ ለሰው ፡ ከድካሙ ፡ በቀር ፡ ትርፉ ፡ ምንድን ፡ ነው
ይልቅ ፡ በጉብዝናው ፡ ወራት ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው (፪x)

ሳይደክሙ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
ሳይጨልም ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
ነፍስም ፡ ሳትወጣ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው

አይ ፡ ጐበዝ ፡ የተባለው ፡ ሰው፡ አገር ፡ ሁሉ ፡ የሚያደንቀው
ጥሮ ፡ ግሮ ፡ ያከማቸውን ፡ ጥሎት ፡ ሄደ ፡ ሳይበላው ፡ ሃብቱን
ይሄም ፡ ከንቱ ፡ መድረሻው ፡ ምንድን ፡ ነው
እድሜውን ፡ ሁሉ ፡ ጠፍሮት ፡ ስንፍናው
እንደተባለ ፡ እንደቀረም ፡ መና ፡ እሱም ፡ ሄደ ፡ ሞት ፡ ቀደመውና

ሳይደክሙ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
ሳይጨልም ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
በሩ ፡ ሳይዘጋ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው
ነፍስም ፡ ሳትወጣ ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው

አዝ፦ ለሰው ፡ ከድካሙ ፡ በቀር ፡ ትርፉ ፡ ምንድን ፡ ነው
ይልቅ ፡ በጉብዝናው ፡ ወራት ፡ ጌታን ፡ ማሰብ ፡ ነው (፪x)