ኤልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል (Elzabielen Wushoch Yibeluatal) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

እግዚአብሔር ፡ ለቤቱ ፡ ቀንቷል
ጠላትን ፡ ያዋርዳል ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል
ነብያትን ፡ ይታደጋል ፡ አያይአሃ
ከእጆችዋም ፡ ያስመልጣል ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይበሏታል

አዝ፦ ማነው ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የሚበቀላት
ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x)
ቀድማ ፡ እራሷን ፡ አስጊጣ ፡ አለች ፡ ሰውን ፡ ልታስት
ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x)

መሸነፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ያብቃ ፡ ዛቻዋን ፡ ሰምቶ ፡ ድበቃ
ውጣና ፡ ተበቀላት ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይብሏት
መሸነፍ ፡ ከእንግዲህ ፡ ያብቃ ፡ ዛቻዋን ፡ ሰምቶ ፡ ድበቃ
ውጪና ፡ ተበቀያት ፡ አልዛቤልን ፡ ውሾች ፡ ይብሏት

አዝ፦ ማነው ፡ ከኔ ፡ ጋር ፡ ያለው ፡ ማነው ፡ የሚበቀላት
ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x)
ቀድማ ፡ እራሷን ፡ አስጊጣ ፡ አለች ፡ ሰውን ፡ ልታስት
ከከፍታዋ ፡ ላይ ፡ ወርውሯት (፪x)

የተኛህ ፡ ንቃ ፡ ቀን ፡ ሳለ
እሷ ፡ እያለች ፡ ምን ፡ ሰላም ፡ አለ
አብረን ፡ እናስወግዳት
አስጥላት ፡ እንዳታነሳት

እኔ ፡ ባለሁበት ፡ ከተማ
አይሰራም ፡ ግልሙትናዋ
እኛም ፡ ባለንበት ፡ መንደር
አይሰልጥን ፡ የእሷ ፡ ነገር