እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው (Egziabhier Feqer New) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ያ ፡ ሰነፍ ፡ ቢመስለው ፡ ያወቀ
ከአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ወጥቶ ፡ ወደቀ
ሄደና ፡ እንዳሻው ፡ እንደልቡ
እስኪረዳ ፡ እንደጣለ ፡ ክብሩን

ተመልሶ ፡ መጣ ፡ በሀዘን
ብሎ ፡ እንደባሪያው ፡ እንኳ ፡ ብሆን
መመለሱን ፡ ያየም ፡ አባቱ
አቀፈው ፡ ልክ ፡ እንደበፊቱ

አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እያሳየ ፡ እየተገበረ (፪x)

ይቺ ፡ ሴት ፡ ኃጢአተኛ ፡ ናት
ህግ ፡ አለህ ፡ አንተም ፡ ፍረድባት
እያሉ ፡ ላመጧት ፡ ለዚያች ፡ ነፍስ
ጠበቁ ፡ ምን ፡ እንደሚመልስ

እርሱ ፡ ግን ፡ እውነቱን ፡ ተናገረ
ሁሉም ፡ ራሱን ፡ እንዲያይ ፡ አረገ
የእሷንም ፡ ፍርዷን ፡ አንስቶላት
አትድገሚው ፡ ልጄ ፡ ሂጂ ፡ አላት

አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እያሳየ እየተገበረ (፪x)

ሁሉ ፡ እንዲድን ፡ አንዷ ፡ እንዳትጠፋ
ቢገደው ፡ ያ ፡ መልካም ፡ እረኛ
በረት ፡ ያሉትን ፡ ይተውና
ይሄዳል ፡ እሷኑ ፡ ፍለጋ

ያሰማታል ፡ ድምጹን ፡ አውጥቶ
በእቅፉ ፡ ሊያስገባት ፡ ጓጉቶ
ነፍሱን ፡ ስለበጐቹ ፡ ያኖረው
እውነተኛ ፡ ፍቅር ፡ እርሱ ፡ ነው

አዝ፦ ኧረ ፡ እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እግዚአብሔር ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ ኧረ
እያሳየ እየተገበረ (፪x)