From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የጭንቁ ፡ ጊዜ ፡ ሳይመጣ ፡ ግዳጅ ፡ ሳይሆንብኝ
አመልካለሁ ፡ በውዴታ ፡ አየተገዛሁ ፡ ለጌታ (፪x)
ግዴታዬን ፡ ለማክበር ፡ አይደለም ፡ የማመሰግነው
ይልቁንም ፡ ፍቅሩ ፡ ጨምሮብኝ ፡ አጣሁኝ ፡ የምለው (፪x)
ሳይወዱ ፡ ጌታ ፡ ነህ ፡ ቢሉት ፡ ቀን ፡ አስገድዷቸው
እኔ ፡ አስቲ ፡ ልዘምርለት ፡ ምቹ ፡ ሳለ ፡ ጊዜው (፪x)
ስንት ፡ የምለው ፡ ነገር ፡ በልቤ ፡ የለኝ
ቃላት ፡ አቅም ፡ አጣ ፡ ተቸገርኩ ፡ እያነሰብኝ
እኔ ፡ ከማቀርበው ፡ እልፍ ፡ የምስጋና ፡ ቃል
የእግዚአብሔር ፡ የአንድ ፡ ቀን ፡ ምሕረቱ ፡ ይመዝንብኛል
የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው
የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው
የሚያሳስበኝ ፡ ጌታን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው
የሚያሳስበኝ ፡ እሱን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው
ነገር ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ኑሮም ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፪x)
አንዳንድ ፡ ጊዜ ፡ አይደለም ፡ የማመሰግነው
ሲጐልም ፡ እሰየሁ ፡ ሲሞላም ፡ እሰየሁ
የማመሰግንበት ፡ ምክንያቴ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው (፪x)
ጌታ ፡ ካለ ፡ ቤቴ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x)
እጠግባለሁ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ (፪x)
እሱ ፡ ካለ ፡ ቤቴ ፡ ሙሉ ፡ ነው (፪x)
እጠግባለሁ ፡ ፊቱን ፡ እያየሁ (፪x)
የሚያሳስበኝ ፡ አንተን ፡ አንዴት ፡ እንደማከብር ፡ ነው
የሚያሳስበኝ ፡ አንተን ፡ አንዴት ፡ እንደማስከብር ፡ ነው (፪x)
አፌን ፡ ሞልቼ ፡ እንድዘምረው
የሚጋብዘኝ ፡ ማንነትህ ፡ ነው (፪X)
ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይድረስህ
ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይኸውልህ
ለማንነትህ ፡ ክብር ፡ ይሁንልህ
ነገር ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ
ኑሮም ፡ ጐደለ ፡ እግዚአብሔር ፡ አለ (፫x)
|