From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አይናፍቀኝም ፡ ሃገሩ ፡ ያ ፡ ጨለማ ፡ ያ ፡ ሃሩሩ
ነፃ ፡ አውጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ በነፃነት ፡ ልኖር ፡ እፎይ ፡ ብዬ (፪x)
አራገፈና ፡ ሸክሜን ፡ ያጎበጠኝን ፡ ቀንበሬን
አሸክሞኛል ፡ የራሱን ፡ የቀለለ ፡ የለዘበውን
አሸክሞኛል ፡ ፍቅሩን ፡ እየገለፀ ፡ ትርጉሙን
አሸክሞኛል ፡ ፀጋውን ፡ እንድመሰክር ፡ ስራውን
አዝ፦ እገዛለታለሁ ፡ በደስታ ፡ አሸንፎኛል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
በሰው ፡ ፍቅር ፡ የወደቀ ፡ እንኳን ፡ ይሰጥ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ እራሱን
ኧኸይ ፡ በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ ኧኸይ ፡ ተጠፍሬያለሁ
ኧኸይ ፡ ውሎ ፡ እያደረ ፡ አያይ ፡ አያይ ፡ ልቤን ፡ እረታው
ሁለት ፡ ጌቶች ፡ አይገዙኝም ፡ ጉዳዬ ፡ ሌላ ፡ አልደብልም
እግዚአብሔር ፡ ስላለው ፡ ብልጫ ፡ አያዳግትም ፡ ለምርጫ
እግዚአብሔር ፡ ስላለው ፡ ብልጫ ፡ አያስቸግርም ፡ ለምርጫ
እግዚአብሔር ፡ ስላለው ፡ ብልጫ ፡ አያዳግትም ፡ ለምርጫ
አዝ፦ እገዛለታለሁ ፡ በደስታ ፡ አሸንፎኛል ፡ ይሄ ፡ ጌታ
በሰው ፡ ፍቅር ፡ የወደቀ ፡ እንኳን ፡ ይሰጥ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ እራሱን
ኧኸይ ፡ በፍቅሩ ፡ ገመድ ፡ ኧኸይ ፡ ተጠፍሬያለሁ
ኧኸይ ፡ ውሎ ፡ እያደረ ፡ አያያዬዬ ፡ ልቤን ፡ እረታው
ዝም ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ
ላገኘሁት ፡ እጄን ፡ እያነሳሁ
አልሟገትም ፡ እያልኩ ፡ ምን ፡ አለበት
የእግዚአብሔር ፡ ፍቃድ ፡ ያልሆነ ፡ እሱ ፡ ሞት ፡ አለበት
አልቀጥፈውም ፡ እጄን ፡ ሰድጄ ፡ ዛሬ
የሚያጠፋ ፡ የሚገ'ለውን ፡ የሞት ፡ ፍሬ
ይቅርብኝ ፡ እንጂ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ጨዋታ
አሳስቆ ፡ ይለይ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ከውዱ ፡ ጌታ (፪x)
ዝም ፡ ብዬ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ
ላገኘሁት ፡ እጄን ፡ እያነሳሁ
አልሟገትም ፡ እያልኩ ፡ ምን ፡ አለበት
የእግዚአብሔር ፡ ፍቃድ ፡ ያልሆነ ፡ እሱ ፡ ሞት ፡ አለበት
አልቀጥፈውም ፡ እጄን ፡ ሰድጄ ፡ ዛሬ
የሚያጠፋ ፡ የሚገ'ለውን ፡ የሞት ፡ ፍሬ
ይቅርብኝ ፡ እንጂ ፡ ከንቱ ፡ ከንቱ ፡ ጨዋታ
አሳስቆ ፡ ይለይ ፡ የለ ፡ ወይ ፡ ከውዱ ፡ ጌታ (፪x)
<poem>
አይናፍቀኝም ፡ ሃገሩ ፡ ያ ፡ ጨለማ ፡ ያ ፡ ሃሩሩ
ነፃ ፡ አውጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ በነፃነት ፡ ልኖር ፡ እፎይ ፡ ብዬ (፪x)
አይናፍቀኝም ፡ ሃገሩ ፡ ያ ፡ ጨለማ ፡ ያ ፡ ሃሩሩ
ነፃ ፡ አውጥቶኛል ፡ ጌታዬ ፡ በነፃነት ፡ ልኖር ፡ እፎይ ፡ ብዬ (፪x)
|