አለኝ ፡ አባት (Alegn Abat) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ሚያስፈልገኝን ፡ ያ'ረገልኝ ፡ ተንከባክቦ ፡ የሚያሳድገኝ
የሚሸከመኝ ፡ እንደልጅነቴ ፡ አለልኝ ፡ ቸሩ ፡ አባቴ (፪x)

አዝ፦ አለኝ ፡ አባት ፡ አባት
የምመካበት ፡ አባት
አለኝ ፡ አባት ፡ አባት
'ማስፈራራበት ፡ አባት

ጠላቴ ፡ ሆይ ፡ ስማ ፡ ወዴት ፡ ወዴት
አትዘንጋው ፡ እንጂ ፡ አንዳለኝ ፡ አባት
እንደ ፡ ዓይኑ ፡ ብሌን ፡ 'ሚያስብ ፡ 'ሚጠነቀቅ
በልጁ ፡ የመጣበትን ፡ የማይምር ፡ የማይለቅ

አዝ፦ አለኝ ፡ አባት ፡ አባት
የምመካበት ፡ አባት
አለኝ ፡ አባት ፡ አባት
ማስፈራራበት ፡ አባት

እግዚአብሔር ፡ አባቴ ፡ እኩያ ፡ የለውም
ግን ፡ እኮ ፡ ማንንም ፡ አይንቅም (፪x)

ይቅርታው ፡ ብዙ ፡ ሁልጊዜ ፡ የሚምር
መልካሙን ፡ መንገድ ፡ የሚያስተምር
ማማክረው ፡ የሚመክረኝ
አባቴ ፡ እያለ ፡ ምን ፡ አባዘነኝ

ሰውን ፡ ተስፋ ፡ ማድረጉ ፡ በቃኝ ፡ በቃኝ
ግራ ፡ ቀኝ ፡ ማየቱ ፡ በቃኝ ፡ በቃኝ

ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ
ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ

መጥቼም ፡ ሸክሜን ፡ አራግፋለሁ ፡ ጌታ
እንደማትሰለቸኝ ፡ ተማምኛለሁ ፡ ጌታ
ሁልጊዜ ፡ የፍቅር ፡ ብሩህ ፡ ፊት ፡ አለህ ፡ ጌታ
የሚያቀርብ ፡ የሚያስጠጋ ፡ ጌታ

ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ
ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ

ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልቆራኝ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ልወዳጅ
ይሄ ፡ ነው ፡ የሚረባ ፡ ይሄ ፡ ነው ፡ የሚበጅ (፬x)

ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ
ጉዳይ ፡ አለኝ ፡ ከአንተ'ጋ ፡ መጥቻለሁ ፡ ላወጋ