አቤት ፡ ውበቱ ፡ የሌሊቱ (Abet Wubetu Yelielitu) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 2.jpeg


(2)

ተፈፀመ
(Tefetseme)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፯ (2005)
ቁጥር (Track):

(8)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አዝ፦ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ
ሲገለጥ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ
አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ
ሲታይ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ

የኑሮዬ ፡ ለሊት ፡ እንዲነጋ ፡ የማውቅበት
የሕይወቴ ፡ ለሊት ፡ ማዳኑን ፡ የማይበት (፪x)

ዝም ፡ ባለው ፡ በድቅድቅ ፡ ለሊት ፡ አጋዥ ፡ በሚያሻበት
ግራ ፡ ቀኝ ፡ እያየሁ ፡ ስጣራ ፡ ፈልጌ ፡ እረዳት
አምላኬ ፡ መንፈሴን ፡ አንቅቶ ፡ አበራልኝ ፡ እውነቱን
በከበበኝ ፡ ጨለማ ፡ መሃል ፡ አሳየኝ ፡ ምሕረቱን

በሰማይ ፡ ያሉ ፡ ከዋክብት ፡ ሲመሽ ፡ እንደሚደምቁት
ዙሪያዬ ፡ ሲጨልምብኝ ፡ የአምላኬን ፡ ማዳን ፡ አየሁት (፪x)

አዝ፦ አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ
ሲገለጥ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ
አቤት ፡ ውበቱ ፡ አቤት ፡ ውበቱ ፡ የለሊቱ
ሲታይ ፡ እውነቱ ፡ ውበት ፡ አለው ፡ ለሊቱ

የኑሮዬ ፡ ለሊት ፡ እንዲነጋ ፡ የማውቅበት
የሕይወቴ ፡ ለሊት ፡ ማዳኑን ፡ የማይበት (፪x)

ሊያባብለኝ ፡ በምድረበዳ ፡ ወሰደኝ
አስተምሮ ፡ አስተካክሎ ፡ ሊቀርፀኝ
በውዴ ፡ ላይ ፡ በርሱ ፡ ብቻ ፡ ተደግፌ
ይህች ፡ ማን ፡ ናት ፡ የሚሉኝን ፡ እንዳይ ፡ አልፌ

ያለኝን ፡ በሙሉ ፡ ወዲያ ፡ ማዶ
አሻገረው ፡ ብቻዬን ፡ ሊያይ ፡ ወዶ
ሲታገለኝ ፡ ቆየ ፡ በጨለማው
አስቸጋሪው ፡ ልቤን ፡ እስክረታው (፪x)

ሥሜን ፡ ሊቀይር ፡ አድኖም ፡ ሊያስቀረኝ
የሁለት ፡ ክፍል ፡ ሰራዊት ፡ ሊያረገኝ
ሥርዓቱን ፡ እማር ፡ ዘንድ ፡ አስጨነቀኝ (፬x)