From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ሰልፉን ፡ አይቼ ፡ ልቤ ፡ ሲርድ
በእጃቸው ፡ ገባሁ ፡ ዛሬ ፡ ሳልወድ
ብዬ ፡ አምላኬን ፡ ምነው ፡ ስል
ትዕዛዝ ፡ አወጣ ፡ እንዲህ ፡ ሲል፦
ማለዳ ፡ ቆሜ ፡ ተራራ ፡ ላይ
ክብሬን ፡ ዘምሪ ፡ ክብር ፡ እንድታዪ
እኔም ፡ ሰምቼው ፡ ስዘምር
ሰደደባቸው ፡ ድብቅ ፡ ጦር
ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እነሳለሁ ፡ ከበሮዬን ፡ አነሳለሁ
ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይርዳል ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት
ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እነሳለሁ ፡ በገናዬን ፡ አነሳለሁ
ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይፈታ ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት
አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ወደ ፡ ጓዳዬ ፡ እንደለመድኩት
ለአምላክ ፡ ስዘምር ፡ እንዳደግኩት
ዛሬ ፡ አደባባይ ፡ ወጣሁና
ሥሙን ፡ ጠራሁት ፡ እንደገና
ብላቴኖችን ፡ የሚወደው
እግዚአብሔር ፡ ቀባኝ ፡ አትበሉ ፡ እንዴት ፡ ነው
ክፉ ፡ መንፈስ ፡ አይቶኝ ፡ ሲሸሽ
ጌታ ፡ ይከብራል ፡ ነግቶ ፡ እስኪመሽ
ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እንነሳለሁ ፡ ከበሮዬን ፡ አነሳለሁ
ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይርዳል ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት
ማልጄ ፡ ሆ ፡ ብዬ ፡ እንነሳለሁ ፡ በገናዬን ፡ አነሳለሁ
ለአምላኬ ፡ ስዘምርለት ፡ ይፈታ ፡ የጠላቴ ፡ ጉልበት
አዝ፦ የዝማሬው ፡ ጉልበት ፡ ያለው ፡ በአፌ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
የዝማሬው ፡ ቅባት ፡ ያለው ፡ በእኔ ፡ ላይ (፪x)
ለአምላኬ ፡ የክብሩ ፡ ሙዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
ለእግዚአብሔር ፡ የክብሩ ፡ ሞዳይ
ለጠላቴ ፡ የበረዶ ፡ ድንጋይ
|