የሰላም ፡ ጥጉ (Yeselam Tegu) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:49
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ
ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ
ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x)

ልብህ ፡ ሲፈካ ፡ እንደ ፡ አበባ
በአገኘው ፡ ነገር ፡ ሲፅናና
ደግሞ ፡ በዚያው ፡ ልክ ፡ የሃዘን ፡ ድባብ
ድብት ፡ ሲያደርገው ፡ ተስፋ ፡ ሲቆርጥ
ስንቱ ፡ ነው ፡ ሚታየው ፡ በሕይወት
ለዚያች ፡ ዕድሜ ፡ ተችሮት
ግን ፡ አዋቂ ፡ ያ ፡ ብልሁ
በአምላክ ፡ ሲሆን ፡ ነው ፡ መደሰቱ

የማይናወጥ ፡ ሰላሜን ፡ ደስታዬን
እኔ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን
የምድር ፡ ስኬት ፡ ሚሰጠው ፡ ምንድን ፡ ነው
ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ባይ ፡ ማን ፡ ነው

አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ
ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ
ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x)

መች ፡ በአንድ ፡ ነገር ፡ ልብ ፡ ይረካል
አንዱ ፡ ሲሰጠው ፡ ሌላ ፡ ይሻል
ያሻውንም ፡ ቢያገኝ ፡ ሰው ፡ ምኞቱ
በቃ ፡ አይልም ፡ አይሞላለት ፡ ቋቱ
ሕይወት ፡ የሚረጋው ፡ በእረፍት
ኢየሱስ ፡ ሲገባ ፡ ወደ ፡ ቤት
የሰላም ፡ ምንጩን ፡ ከተጠጉ
ሌላ ፡ ደስታ ፡ አይፈልጉ

የማይናወጥ ፡ ሰላሜን ፡ ደስታዬን
እኔ ፡ አግኝቻለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታዬን
የምድር ፡ ስኬት ፡ ይሰጠው ፡ ምንድን ፡ ነው
ከኢየሱስ ፡ ሌላ ፡ ደስታ ፡ አለ ፡ ባይ ፡ ማን ፡ ነው (፪x)

አዝ፦ ሰው ፡ በምን ፡ ይረካል ፡ ልቡ
ዓለሙም ፡ አያልፍም ፡ ልኩ
ጌታ ፡ ነው ፡ የሰላም ፡ ጥጉ (፪x)
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ የደስታ ፡ ጥጉ (፪x)