የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (Yenie Gieta New) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ሞገስ ፡ የጠገበ ፡ ክብር ፡ የተረፈው
ምሥጋና ፡ አምልኮ ፡ ገንዘቡ ፡ የሆነው
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

ሰማይ ፡ ምድሩ ፡ የተገረመበት
ለውበቱ ፡ የተነገረለት
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ክብሩ ፡ ሰማያትን ፡ የከደነ
ምሥጋናው ፡ በምድር ፡ የተነነ
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ጌታ ፡ የኃያላን ፡ ጌታ
የአለቆች ፡ ጌታ ፡ የመሪዎች ፡ ጌታ ፡ የብርቱዎች ፡ ጌታ (፪x)

እግዚአብሔር ፣ እግዚአብሔር
የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እርሱማ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እርሱማ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

አዶናይ ፡ ፀባዖት ፡ ኤልካዶሽ ፡ የሆነው
ራሱን ፡ ተማምኖ ፡ አውቆ ፡ እኔ ፡ ነኝ ፡ ያለው
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

ሰማያትን ፡ በስንዝር ፡ የለካ
ዓለማትን ፡ በእጆቹ ፡ የያዘው
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)
ከዋክብትን ፡ በሥም ፡ የሚጠራ
በቀን ፡ በሌት ፡ ሁሉን ፡ የሚያሰማራ
እርሱማ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ነው (፪x)

የጌታዎች ፡ ጌታ ፡ የነገሥታት ፡ ጌታ ፡ የኃያላን ፡ ጌታ
የአለቆች ፡ ጌታ ፡ የመሪዎች ፡ ጌታ ፡ የብርቱዎች ፡ ጌታ (፪x)

እግዚአብሔር ፣ እግዚአብሔር
የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እርሱማ ፡ እግዚአብሔር (፪x)

የእኔ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ እርሱማ ፡ እግዚአብሔር (፪x)