የእግዚአብሔር ፡ እጅ (YeEgziabhier Ej) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(9)

ርዝመት (Len.): 5:35
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ የያዘው ፡ ነገር
እንዳይወድቅ ፡ አይፈራ ፡ እንዳይጠፋ ፡ አይፈራ
ከጥላው ፡ ሥር ፡ ያረፈው ፡ ሰው
ዘላለሙ ፡ አያሰጋው (፪x)

አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x)
ኑሮዬ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x)
አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ ከለላዬ
በጥላህ ፡ ሥር ፡ ነው ፡ ማደሪያዬ (፪x)

በእናቴ ፡ ማህፀን ፡ ደም ፡ ሳለሁኝ ፡ አጥንቶቼም ፡ ሳይዋደዱ
አንተው ፡ ታውቀው ፡ ነበር ፡ እንዲህ ፡ እንዲሆን ፡ የሕይወቴ ፡ አካሄዱ
ደግሞስ ፡ ካሳለፍከኝ ፡ በቸርነትህ ፡ የትላንቱን ፡ ጨለማ
ለነገውስ ፡ ቢሆን ፡ ለምን ፡ አላምንም ፡ ሕይወቴ ፡ በእጅህ ፡ ነውና

ተውኩት ፡ ሁሉንም ፡ ለአንተ ፡ ተውኩት
ተይ ፡ ነፍሴ ፡ እኔ ፡ አላውቅም ፡ ብዬ ፡ እንዳልኩት
ይሁን ፡ ያልከው ፡ የፀና ፡ ለመሆኑ
ምስክር ፡ ነው ፡ ሰማይ ፡ የለ ማዕገር መቆሙ

አዝ፦ የእግዚአብሔር ፡ እጅ ፡ የያዘው ፡ ነገር
እንዳይወድቅ ፡ አይፈራ ፡ እንዳይጠፋ ፡ አይፈራ
ከጥላው ፡ ሥር ፡ ያረፈው ፡ ሰው
ዘላለሙ ፡ አያሰጋው (፪x)

አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ወዳጅ (፪x)
ኑሮዬ ፡ በአንተ ፡ እጅ (፪x)
አባትዬ ፡ የእኔ ፡ ከለላ ፡ ከለላዬ
በጥላህ ፡ ሥር ፡ ነው ፡ ማደሪያዬ (፪x)

ክብርን ፡ የምትገልፅበት ፡ ደካማ ፡ ሰው ፡ ስትፈልግ ፡ አገኘኸኝ
እንጂማ ፡ በእራሴ ፡ እንኳን ፡ በአንተ ፡ በሰውም ፡ ዓይን ፡ የማልሞላ ፡ ነኝ
ግና ፡ ከወደድከኝ ፡ በዓይነህ ፡ ከታየሁ ፡ እኔስ ፡ ምን ፡ እልሃለሁ
አንተ ፡ ነህ ፡ ደጀኔ ፡ ተባረክልኝ ፡ ከትከሻህ ፡ የሚያወርደኝ ፡ ማነው

አልጥልሽ ፡ አልተውሽ ፡ እያልክ
ልቤን ፡ ስትደግፈኝ ፡ እንደዋልክ
አይቼህ ፡ መንፈሴ ፡ ረካ
አትተወኝም ፡ አትረሳኝም ፡ ለካ
አዬ ፡ አትረሳኝም ፡ ለካ

አትተወኝም ፡ በቃ ፡ አትረሳኝም ፡ በቃ
አሄ ፡ አትረሳኝም ፡ በቃ
አትተወኝም ፡ በቃ ፡ አትለቀኝም ፡ በቃ
አሄ ፡ አትለቀኝም ፡ በቃ (፪x)