From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ልቤ ፡ ዋተተ ፡ ዋተተ
መንፈሴም ፡ ታወከብኝ
ልጄ ፡ አንተን ፡ አጥቼ ፡ ከጉያዬ
እንዴት ፡ ልረፍ ፡ በምን ፡ anjet chye
እህ ፡ እህህህህ
እህህ ፡ ሆነብኝ ፡ ጠዋት ፡ ማታ
ወንድሞችህ ፡ ቢኖሩም ፡ በቤት
አይተኩትም ፡ ለአንተ ፡ ያለኝን ፡ ቦታ
አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ
ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ
ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x)
ደጅ/በር ፡ አፍ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ያንኳኳል ፡ ወዳጅ
ይጣራል ፡ ወዳጅ (፪x)
ድምጹን ፡ ሲያሰማ ፡ አስገባው ፡ ከፍተህ
አይጥና ፡ ደጅ ፣ አይጥና ፡ ደጅ (፪x)
እናት ፡ ትረሳ ፡ ይሆናል ፡ አምጣ ፡ የወለደችውን
እኔማ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ነው ፡ እንዴት
አንተን ፡ ጥሎ ፡ መኖር ፡ በሞቀ ፡ ቤት
ልጄን ፡ ካልያዝኩት ፡ አልረካ
ክርትት ፡ አለ ፡ ዓይኔ ፡ አንተን ፡ ፍለጋ
ወድሃለሁ ፡ ልጄ ፡ ናና ፡ ናና
ሙሉ ፡ እንዲሆን ፡ የቤቴ ፡ ምሥጋና
አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ
ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ
ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x)
ደጅ/በር ፡ አፍ ፡ ላይ ፡ ቆሞ ፡ ያንኳኳል ፡ ወዳጅ
ይጣራል ፡ ወዳጅ (፪x)
ድምጹን ፡ ሲያሰማ ፡ አስገባው ፡ ከፍተህ
አይጥና ፡ ደጅ ፣ አይጥና ፡ ደጅ (፪x)
አባ ፡ አባባ ፡ ስትለኝ
እስቲ ፡ ልስማህ ፡ ያ ፡ ድምጽህ ፡ ናፈቀኝ
ሸክምህን ፡ አውርድ ፡ ከጫንቃህ
ላሳርፍህ ፡ አለሁ ፡ አባትህ
የሚያሳየው ፡ ጐልጐታ
ዛሬም ፡ ያው ፡ ነው ፡ ፍቅሬ ፡ መች ፡ ተገታ
በላ ፡ እንሂድ ፡ ወደ ፡ ቤታችን
እኔም ፡ ልረፍ ፡ አግኝቼ ፡ አንተን
አዝ፦ ወዴት ፡ አለህ
ድምጼን ፡ ሰምተህ ፡ አለሁ ፡ በለኛ
ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ
(ወዴት ፡ አለህ) ፡ ወዴት ፡ አለህ
(ድምጼን ፡ ሰምተህ) ፡ ድምጼን ፡ ሰምተህ
አለሁ ፡ በለኛ ፡ (አለሁ ፡ በለኛ)
ፈጠን ፡ ብለህ ፡ ወደ ፡ እቅፌ ፡ ግባ (፪x)
|