From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
አዝ፦ አንደበቱን ፡ የሚገታ ፡ ሰውነቱን ፡ ይገዛልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
አንደበቱን ፡ የሚጠብቅ ፡ ነፍሱን ፡ ይጠብቃታልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
አመጸኛ ፡ አለ ፡ ሙሉ ፡ ሥጋውን ፡ ያሳድፋል
ትንሽ ፡ እሳት ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ትልቅ ፡ ጫካ ፡ ያጋያል
ከአንድ ፡ ምንጭ ፡ መራርና ፡ ጣፋጭ ፡ እንዳይቀዳ
ከአንደበትህ ፡ አንዴ ፡ መርገም ፡ አንዴ ፡ ባርኮት ፡ አይውጣ
ፈዋሽ ፡ ምላስ ፡ የሕይወት ፡ ዛፍ ፡ ናት
መልካም ፡ ፍሬ ፡ ሚለቀምባት
የጠቢብ ፡ ቃል ፡ እንደምንጭ ፡ ነው
የተፍገመገመውን ፡ የሚያቀናው (፪x)
አዝ፦ አንደበቱን ፡ የሚገታ ፡ ሰውነቱን ፡ ይገዛልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
አንደበቱን ፡ የሚጠብቅ ፡ ነፍሱን ፡ ይጠብቃታልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
መልካም ፡ ዘመን ፡ ማየት ፡ ካሻህ ፡ አፍህን ፡ ከክፉ ፡ ከልክል
በቃል ፡ ብዛት ፡ ኃጢአት ፡ ሳይኖር ፡ አይቀርምና ፡ አስተውል
ልብ ፡ የሞላውን ፡ ያንኑ ፡ አፍ ፡ ይናገራልና
ጆሮህን ፡ ለትምህርት ፡ አቅና ፡ ጥበብ ፡ ልብህን ፡ ይሙላ
ፈዋሽ ፡ ምላስ ፡ የሕይወት ፡ ዛፍ ፡ ናት
መልካም ፡ ፍሬ ፡ ሚለቀምባት
የጠቢብ ፡ ቃል ፡ እንደምንጭ ፡ ነው
የተፍገመገመውን ፡ የሚያቀናው (፪x)
አዝ፦ አንደበቱን ፡ የሚገታ ፡ ሰውነቱን ፡ ይገዛልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
አንደበቱን ፡ የሚጠብቅ ፡ ነፍሱን ፡ ይጠብቃታልና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
የሕይወት ፡ ቃል ፡ መውጫ ፡ በር ፡ ናትና
ዘሯም ፡ ሲያፈራ ፡ እጥፍ ፡ ነውና
ለአፍህ ፡ ጠባቂ ፡ አኑር
|