From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ቀን ፡ ጠብቆ ፡ ገሸሽ፡ ይልብኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ?
አለልኝ ፡ ስል ፡ ዓይንሽ/ህ ፡ ለአፈር ፡ ይለኛል ፡ ወይ?
ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም
ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም (፪x)
እርሱማ ፡ እየበደልኩት ፡ ቻለኝ
እርሱማ ፡ እየራቅኩት ፡ ቀረበኝ
እርሱማ ፡ ሰለቸኝ ፡ ወዲያ ፡ አላለኝ (፪x)
ብሸሸው ፡ ብርቀው ፡ አለቅ ፡ ያደረገኝ
ጌታ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?!
ከ'ነማንነቴ ፡ የወደደኝ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! (፪x)
እያባበለኝ (፫x)
ተሸከመኝ (፫x)
በምክሩም ፡ ሲያስተምረኝ ፡ ደጉን ፡ ሲያሰየኝ
እንደ ፡ አባት ፡ ሲቀጣኝ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ አወኩኝ
መልሶ ፡ ሲያባብለኝ ፡ አለው ፡ ሲለኝ ፡ ሲያበረታታኝ
ፍቅር ፡ ማለት ፡ ምን ፡ እንደሆነ ፡ አወ'ኩኝ (፪x)
እያባበለኝ (፫x)
ተሸከመኝ (፫x)
ቀን ፡ ጠብቆ ፡ ገሸሽ ፡ ይልብኝ ፡ ይሆን ፡ ወይ?
አለልኝ ፡ ስል ፡ ዓይንሽ/ህ ፡ ለአፈር ፡ ይለኛል ፡ ወይ?
ብዬ ፡ እንዳልል ፡ እንዳልሰጋበት ፡ ዛሬም
አብሮኝ ፡ አለ ፡ ቤቴ ፡ ባይመቸውም (፪x)
እርሱማ ፡ እየበደልኩት ፡ ቻለኝ
እርሱማ ፡ እየራቅኩት ፡ ቀረበኝ
እርሱማ ፡ ሰለቸኝ ፡ ወዲያ ፡ አላለኝ (፪x)
ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ነጥቆ ፡ ተስፋን ፡ የጨመረልኝ
ጌታ ፡ አይደል ፡ ወይ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?!
የተቆረጠውን ፡ የቀጠለልኝ ፡ ጌታ ፡ አይደለም ፡ ዎይ?! (፪x)
እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ ፣ እያባበለኝ
ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ ፣ ተሸከመኝ (፫x)
|