From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
የሹዋ ፡ ሮሓሚን
ኤል ፡ ሮሓሚን
አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ
ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ
ላያስበው ፡ መልሶ
እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ
ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x)
አላውቀውም ፡ ቢል ፡ ቢምል ፡ ቢክድም
ራሱን ፡ ሊያድን ፡ ራሱን ፡ ቢወድም
መልሶ ፡ ሲያዝን ፡ ሲፀፀት ፡ አየው
የመንግሥቱን ፡ ቁልፍ ፡ በእጁ ፡ አስጨበጠው
ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል
ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል
የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ
ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x)
አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ
ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ
ላያስበው ፡ መልሶ
እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ
ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x)
ኃጢአት ፡ ቢያደርግም ፡ ምልስ ፡ ልብ ፡ ይዟል
የምህረቱን ፡ ደጅ ፡ ፈጥኖ ፡ ያንኳኳል
የተጻፈልን ፡ ለትምህርት ፡ ነው
ምስክሩ ፡ ግን ፡ እንደ ፡ ልቤ ፡ ነው
ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል
ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል
የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ
ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x)
አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ
ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ
ላያስበው ፡ መልሶ
እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ
ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x)
ድርሻውን ፡ ወስዶ ፡ ትቶ ፡ ቢወጣ
እንዲያው ፡ ሲባዝን ፡ መቅኖውን ፡ አጣ
ባሪያ ፡ ልሁን ፡ ሲል ፡ ዕድል ፡ ካገኘሁ
የጠበቀው ፡ ግን ፡ ልጅነቱ ፡ ነው
ጌታ ፡ ይምራል ፡ ጌታ ፡ ይረሳል
ኃጢአትን ፡ ደግሞ ፡ መቼ ፡ ያስታውሳል
የማረኝ ፡ ነኝ ፡ የተወልኝ
ላያወሳው ፡ ላይደግምብኝ (፪x)
አዝ፦ ሲምር ፡ ይምራል ፡ ጌታ
ሳያቅማማ ፡ ለአፍታ
ላያስበው ፡ መልሶ
እንባን ፡ ከዓይን ፡ አብሶ
ይቅር ፡ ይላል ፡ ፈውሶ (፪x)
አዶናይ ፡ ሮሆሚን
ራፋዬል ፡ ሮሆሚን
መሲያሕ ፡ ሮሆሚን
ኤል ፡ ሮሆሚን
አዶናይ ፡ ሮሆሚን
የሱዋ ፡ ሮሆሚን
|