ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ (Edmieyie Bebieteh Yileq) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 5:45
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ቤትህን ፡ ሊሰራ ፡ የተመረጠው
የተወደደ ፡ ጥበብ ፡ የሞላው (፪x)
ክብር ፡ ሲሆንለት ፡ ዝና ፡ ሲተርፈው
የአባቶቹን ፡ አምላክ ፡ እንደማያውቀው
ጣዖት ፡ አምልኮ ፡ ሞት ፡ ሆነ ፡ ፍጻሜው

አዝ፦ ዕድሜዬ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ
ይለቅልኝ ፡ በፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ
ይመርልኝ ፡ በፊትህ

ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ
ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ
ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x)

አህያ ፡ ፍለጋ ፡ ተልኮ ፡ ቢወጣ
እጣ ፡ ወደቀበት ፡ ህዝብን ፡ እንዲመራ
ከፍልስጤማዊ ፡ ነጻ ፡ እንዲያወጣ

ደርሶ ፡ ንጉሥ ፡ ሲሆን ፡ ትህትና ፡ አጣ
ክፉ ፡ መንፈስ ፡ ያዘው ፡ ከአንተ ፡ መንገድ ፡ ወጣ
መውደቂያው ፡ ሆነበት ፡ የጊልቦዓ ፡ ተራራ

አዝ፦ ዘመኔ ፡ ይለቅልኝ ፡ ቤትህ
ይለቅልኝ ፡ በፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመርልኝ ፡ ፊትህ
ይመርልኝ ፡ በፊትህ

ሩጫዬ ፡ እንዳይገታ
ጠብቀኛ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
እኔ ፡ እንዳልሆን ፡ ለእኔው ፡ ጠላቴ
ሰውረኝ ፡ ከዓይን ፡ አምሮቴ (፪x)

በትንሳኤው ፡ ጉልበት ፡ ዓይናቸው ፡ የበራ
ጨከኑ ፡ በሕይወት ፡ ለሰሙት ፡ አደራ
ቤታቸውን ፡ ሰጡ ፡ ለወንጌል ፡ አደራ

አርበኞች ፡ ሆነዋል ፡ እስሩም ፡ ቢጠና
ነገሥታት ፡ ፊት ፡ ቆሙ ፡ ወንጌልን ፡ ሰበኩና
ሰማዕት፡ ሆነው ፡ አለፉ ፡ ዋጋ ፡ ተመኑና

ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ
ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ
መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ
ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ (፪x)

ድል ፡ ለነሳው ፡ ከሕይወት ፡ አክሊል ፡ ታቀዳጃለህ
ድል ፡ ለነሳው ፡ በቤትህ ፡ እንዲኖር ፡ ትሾመዋለህ
ጅማሬዬ ፡ እንዳማረልኝ ፡ ፍጻሜዬም ፡ ይስመርልኝ
መዝገብ ፡ ላከማች ፡ በሠማይ ፡ ቤትህ
ብል ፡ በማይበላው ፡ በሌለበት

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ሕይወቴ ፡ ይመር ፡ እፊትህ

ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ውበቴ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዕድሜዬ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ
ሳታፍርብኝ ፡ እንድቆም ፡ ፊትህ
ዘመኔ ፡ ይለቅ ፡ እቤትህ