From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
ስለ ፡ ዛሬ ፡ የምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
በየማለዳው ፡ የምረዳው
ዕለት ፡ በዕለት ፡ የሚታይ ፡ እውነት (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ
እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x)
ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት
እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x)
ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት
ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x)
ያለጠፋሁት ፡ በምን ፡ ምክኒያት
ከቦኝ ፡ እንጂ ፡ የአንተ ፡ ምህረት
እያለፈ ፡ እየተከተለኝ
ክፉዉን ፡ ሁሉ ፡ ጥግ ፡ አስያዘልኝ
የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ
ደግነትህን ፡ ይመስክር
በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ
ሕይወቱ ፡ መስመር (፪x)
አልጣለኝም ፡ ደጋግ ፡ እጆችህ
ፍቅር ፡ ናቸው ፡ ዛሬም ፡ ዓይኖችህ
ለዘለዓለም ፡ ቤትህ ፡ እኖራለሁ
ወደኸኛል ፡ እስከ ፡ መጨረሻው
የደረስክለት ፡ ያውራ ፡ እስኪ ፡ ያውራ
ደግነትህን ፡ ይመስክር
በአንተ ፡ የቀናለት ፡ አሃ
የሕይወቱ ፡ መስመር (፪x)
ስለ ፡ ዛሬ ፡ የምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ መልስ ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
ስለ ፡ ነገስ ፡ ምን ፡ ታውቂያለሽ ፡ ቢሉኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ አንድ ፡ ዕውቀት ፡ አለኝ
በእውነት ፡ በእርግጠኛነት
አለ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ቸርነት
በየማለዳው ፡ የምረዳው
ዕለት ፡ በዕለት ፡ የሚታይ ፡ እውነት (፪x)
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ እንደ ፡ ሌለ
እግዚአብሔር ፡ ቸር ፡ እንደሆነ (፪x)
ቸር ፡ ባይሆን ፡ ባለ ፡ ምህረት
እኔ/አንዷ ፡ ነበርኩ ፡ ከሚጠፉት (፪x)
ለክፉዎችም ፡ ቸር ፡ ለማያመሰግኑት
ለሚወዱትም ፡ ቸር ፡ ለሚያምኑበት (፪x)
|