አልዋሽህም (Alwashehem) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 6:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አልዋሽህም ፡ ልቤን ፡ ታያለህና
አልዋሽህም ፡ የልብ ፡ አምላክ ፡ ነህ ፡ እላለሁ
እርቦኛል ፡ በእውነት ፡ ፊትህ ፡ መፍሰስ
ላምልክህ ፡ ይርዳኝና ፡ መንፈስህ

ከስሬ ፡ ደርቼ ፡ ድሪቶዬን
ከላይ ፡ ምለብሰው ፡ የፀዳውን
ሰው ፡ እንደው ፡ የሚያየው ፡ ፊቴ ፡ ፊቴን
እከልላለሁ ፡ ገበናዬን (፪x)

ግን ፡ አንተ ፡ አትዋሽም ፡ አትታለል
ዓይንህ ፡ ዘልቆ ፡ ልብን ፡ ያያል
ዓይንህ ፡ ዘልቆ ፡ ልብን ፡ ያያል (፪x)

የቀድሞውን ፡ ፍቅር ፡ አጣሁት ፡ ፈላልጌ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ማደጌ
ኧረ ፡ እኔስ ፡ ፈራሁኝ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ፡ ማደጌ
የእግዚአብሔርን ፡ ደጅ ፡ እንዳልጠናሁኝ
ዛሬማ ፡ ላፍታ ፡ እንኳ ፡ አቅም ፡ አጣሁ (፪x)

ናፈቀኝ ፡ የጥንቱ ፡ ክብር
ናፈቀኝ ፡ ቤቴ ፡ የነበረ
ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እግዚአብሔር
ናፈቀኝ ፡ ረሃቤ ፡ ትጋቴ
ናፈቀኝ ፡ ትንሿ ፡ ጐጆዬ
ናፈቀኝ ፡ ያ ፡ ፀሎቴ

የተገለጠው ፡ ማንነቴ
ይኸው ፡ በፊትህ ፡ መድኃኒቴ
አቅም ፡ አጣሁኝ ፡ አግዘኝ
ያዘኝ ፡ ኃይልህን ፡ አልብሰኝ (፪x)

ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ፍቅር ፡ ትኩስ ፡ የማይበርድ
በልቤ ፡ የሚኖር ፡ ሁል ፡ ጊዜ ፡ የሚነድ (፪x)
መስሎኝ ፡ እንዳልነበር ፡ በልጅነቴ ፡ ወራት
ራሴን ፡ አገኘሁት ፡ ልምድ ፡ ሆኖብኝ ፡ ቀላት
ቤቴን ፡ አዘረፍኩት ፡ ከፍቼ ፡ ለጠላት

ናፈቀኝ ፡ ለቃልህ ፡ ያለኝ ፡ ቦታ
ናፈቀኝ ፡ ያንን ፡ የእሺታ
ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እርዳኝ ፡ ጌታ
ናፈቀኝ ፡ ለአንተ ፡ ያለኝ ፡ ክብር
ናፈቀኝ ፡ ሥምህ ፡ ሲነገር
ናፈቀኝ ፡ ኦ ፡ እግዚአብሔር

የተገለጠው ፡ ማንነቴ
ይኸው ፡ በፊትህ ፡ መድኃኒቴ
አቅም ፡ አጣሁኝ ፡ አግዘኝ
ያዘኝ ፡ ኃይልህን ፡ አልብሰኝ (፪x)

ይቅር ፡ ይቅር ፡ ይቅርብኝ ፡ ልመልስ
ወደ ፡ ልብህ ፡ ወደ ፡ ሀሳብህ ፡ ልድረስ
ልሸከመው ፡ የመስቀልህን ፡ ፍቅር
ተመልሼ ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ እንዳልቀር
አድስልኝ ፡ የቀድሞውን ፡ ዘመን
ናፍቆት ፡ ሆኖ ፡ ምኞት ፡ ሆኖ ፡ እንዳይቀር
ሰምቼ ፡ አንተን ፡ እንዳፈራበት
ለም ፡ አድርገው ፡ የልቤን ፡ መሬት (፪x)