From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
እኔ
እኔ ፡ እኔ
ዛሬም ፡ እኔ ፡ ነገም ፡ እኔ
ወሬ ፡ እኔ ፡ ስጠኝ ፡ ለእኔ
ልመናዬም ፡ እኔ (፬x)
እዎይ ፡ አልጠግብ ፡ ወይነቴ
አዎይ ፡ አልረካም ፡ ወይነቴ
አዝ፦ አንተ ፡ የሞትክልኝ ፡ ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ
ከሠማዩ ፡ ክብር ፡ እንድሆን ፡ ተካፋይ
እኔ ፡ እዚህ ፡ ስዳክር ፡ ልጨብጥ ፡ ምድርን
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መምሰል
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መውደድ
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
ሊበሉ ፡ የመጡ ፡ ለእንጀራቸው
ሊፈወሱ ፡ ብለው ፡ ለጤናቸው
አመስግነው ፡ ባርከው ፡ ሳይበቃቸው
ተከተሉ ፡ እያሉ ፡ ስቀለው ፡ ስቀለው
አዝ፦ አንተ ፡ የሞትክልኝ ፡ ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ
ከሠማዩ ፡ ክብር ፡ እንድሆን ፡ ተካፋይ
እኔ ፡ እዚህ ፡ ስዳክር ፡ ልጨብጥ ፡ ምድርን
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መምሰል
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መውደድ
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እኔ ፡ እኔ
ዛሬም ፡ እኔ ፡ ነገም ፡ እኔ
ወሬ ፡ እኔ ፡ ስጠኝ ፡ ለእኔ
ልመናዬም ፡ እኔ (፬x)
እዎይ ፡ አልጠግብ ፡ ወይነቴ
አዎይ ፡ አልረካም ፡ ወይነቴ
አዝ፦ አንተ ፡ የሞትክልኝ ፡ ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ
ከሠማዩ ፡ ክብር ፡ እንድሆን ፡ ተካፋይ
እኔ ፡ እዚህ ፡ ስዳክር ፡ ልጨብጥ ፡ ምድርን
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መምሰል
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መውደድ
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እንዲያገለግሉት ፡ ቢጠራቸው
ከባርነት ፡ ፈትቶ ፡ ቢለቃቸው
ሆዳቸው ፡ አምላካቸው ፡ ሆነባቸው
ሥጋ ፡ በልተው ፡ ሞቱ ፡ ሜዳ ፡ ቀረ ፡ ሬሳቸው
አዝ፦ አንተ ፡ የሞትክልኝ ፡ ጐልጐታ ፡ አናት ፡ ላይ
ከሠማዩ ፡ ክብር ፡ እንድሆን ፡ ተካፋይ
እኔ ፡ እዚህ ፡ ስዳክር ፡ ልጨብጥ ፡ ምድርን
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መምሰል
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
እንዳልቀር ፡ አንተን ፡ መውደድ
እንዴት ፡ ነው ፡ ልማር
አንድ ፡ ነገር ፡ እለምንህ ፡ እንድትረዳኝ
እንጀራ ፡ ሰጥተኸኝ ፡ እንዳትሄድብኝ
አንድ ፡ ነገር ፡ እሻለሁኝ ፡ እንድትረዳኝ
እንጀራ ፡ አብልተኸኝ ፡ እንዳትሄድብኝ (፫x)
|