አልቀርም ፡ በመና (Alqerem Bemena) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 3.jpg


(3)

ዕድሜዬ ፡ በቤትህ ፡ ይለቅ
(Edmieyie Bebieteh Yileq)

ዓ.ም. (Year): ፲ ፱ ፻ ፺ ፱ (2007)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 5:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አዝ፦ አደባባይ ፡ ላይ ፡ ሊገለኝ ፡ የማለ
ነግቶለት ፡ እስኪያየው ፡ ልቡ ፡ እንደማለለ
ሃማ ፡ ተሰቀለ (፪x) [1]

አልቀርም ፡ በመና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ መጥናቴ
እግዜር ፡ ለድሆቹ፡ ደራሽ ፡ ነው ፡ ማለቴ (፪x)
በሀዘን ፡ ተመቶ ፡ ልቤ ፡ እንባ ፡ ሲያነባ
ደጁ ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ ስርድ : አየኝና

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ራራልኛ
ጌታዬ ፡ ራራልኛ (፪x)

የቀደመ ፡ መስሎት ፡ ጠላቴ ፡ ማልዶ ፡ ሲያስር ፡ ደባ
አስጨመረልኝ ፡ ሞገስ ፡ አስደረበልኝ ፡ ካባ (፪x)
የረቀቀ ፡ መስሎት ፡ ጠላቴ ፡ ማልዶ ፡ ሲያስር ፡ ደባ
አስጨመረልኝ ፡ ሞገስ ፡ አስደረበልኝ ፡ ካባ (፪x)

ጌታ ፡ ከላይ ፡ ቀደመ ፡ አዋጅ ፡ በአዋጅ ፡ ተሻረ ፡ ሆ
ለእኔም ፡ ፀሐይ ፡ ወጣልኝ ፡ ነጋ ፡ ሌቱ ፡ ነጋልኝ (፪x)

አዝ፦ አደባባይ ፡ ላይ ፡ ሊገለኝ ፡ የማለ
ነግቶለት ፡ እስኪያየው ፡ ልቡ ፡ እንደማለለ
ሃማ ፡ ተሰቀለ (፪x) [1]

አልቀርም ፡ በመና ፡ ደጁ ፡ ላይ ፡ መጥናቴ
እግዜር ፡ ለደሆቹ ፡ ደራሽ ፡ ነው ፡ ማለቴ (፪x)
በሀዘን ፡ ተመቶ ፡ ልቤ ፡ እንባ ፡ ሲያነባ
ደጁ ፡ ላይ ፡ ቁጭ ፡ ብዬ ፡ ስርድ፡ አየኝና

የእኔ ፡ ጌታ ፡ ራራልኛ
ጌታዬ ፡ ራራልኛ (፪x)

አምላክ ፡ አለኝ ፡ የታመኑትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የለመኑትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያመልኩትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚወዱትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)

አምላክ ፡ አለኝ ፡ የታመኑትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የለመኑትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚያመልኩትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)
አምላክ ፡ አለኝ ፡ የሚወዱትን ፡ ሜዳ ፡ የማይጥል (፪x)

ሲያልምልኝ ፡ ቢያድር ፡ ጠላቴ ፡ እንዴት ፡ ማጥ ፡ እንድገባ
አስጨመረልኝ ፡ ሞገስ ፡ አስደረበልኝ ፡ ካባ
አስጨመረልኝ ፡ ሞገስ ፡ አስደረበልኝ ፡ ካባ (፪x)

ጌታ ፡ የምስኪን ፡ ደራሽ
እንባ ፡ ጸሎትን ፡ መላሽ ፡ ኦ
ሰማ ፡ ሰምቶ ፡ መጣልኝ
ደርሶ ፡ ሳቅ ፡ አረገልኝ ፡ ሆ (፪x)

ያስጥላል ፡ በመላ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ አውሬ ፡ እንዳይበላ (፪x)
አለው ፡ ምህረትህ ፡ ለጸኑት ፡ ባለመነሳት
አለው ፡ ምህረትህ ፡ ለጸኑት ፡ ባለመነሳት (፪x)

  1. 1.0 1.1 አስቴር ፯ ፡ ፲ (Esther 7:10)