የሕይወት ፡ እንጀራ (Yehiwot Injera) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)

ርዝመት (Len.): 4:57
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

አንተ ፡ የሕይወት ፡ እንጀራ ፡ ነህ
አንተ ፡ የሕይወት ፡ ብርሃን (፪x)
ታጠግባለህ ፡ ታረካለህ
ታጠግባለህ ፡ ታረካለህ (፪x)

ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ
ወዴት ፡ እሄዳለሁ (፪x)
ተስፋዬ ፡ ነህ ፡ አንተን ፡ እጠጋለሁ (፪x)
አምላኬ ፡ ነህ ፡ አንተን ፡ እጠጋለሁ ፡ የሙጥኝ ፡ ይዣለሁ

ያንን ፡ ትቼ ፡ ይህንን ፡ ትቼ
አንተን ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ (፪x)
ለአንተ ፡ ለመኖር ፡ መጥቻለሁ
አንተን ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ

ያንን ፡ ትቼ ፡ ይህንን ፡ ትቼ
ላገለግልህ ፡ መጥቻለሁ
ለአንተ ፡ ለመኖር ፡ መጥቻለሁ
አንተን ፡ ላከብርህ ፡ መጥቻለሁ
አንተን ፡ ላመልክህ ፡ መጥቻለሁ

አማራጬ/አባቴ ፡ አይደለህ
ብቸኛ ፡ መንገዴ ፡ ነህ
ብቸኛ ፡ መንገዴ ፡ ነህ (፪x)

ያለ ፡ አንተማ ፡ እንዴት ፡ ሊሆንልኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ ምንም ፡ አያምርብኝ
ያለ ፡ አንተማ ፡ ሁሉም ፡ ከንቱ ፡ ነው
ያለ ፡ አንተማ ፡ ኑሮም ፡ ትርጉም ፡ ይለው

ያለ ፡ አንተማ ፡ መውጣት ፡ መግባት ፡ የለም
ያለ ፡ አንተማ ፡ መንገዱም ፡ አይቀና
ያለ ፡ አንተማ ፡ እንዲያው ፡ መቅበዝበዝ ፡ ነው
ያለ ፡ አንተማ ፡ መና ፡ መቅረት ፡ ነው

ታዲያ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወደ ፡ ማን
ትውት/እርግፍ ፡ አድርጊያለሁ ፡ ሌላውን (፪x)

ትዝታም ፡ የለኝም ፡ ትውስታም ፡ የለኝም
ከተውቁት/ካልሆንኩት ፡ ውስጥ ፡ አንዱም ፡ አይቆጨኝም (፪x)

አንተን ፡ አይቶ ፡ ልቤ ፡ አረፈልኝ
እዚህም ፡ እዚያም ፡ ማለት ፡ ቀረልኝ (፪x)

ታዲያ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወደ ፡ ማን
ትውት ፡ አድርጊያለሁ ፡ ሌላውን
ታዴያ ፡ ከአንተ ፡ ወዴት ፡ ወደ ፡ ማን ፡ ኦሆ
እርግፍ ፡ አድርጊያለሁ ፡ ሌላውን