ውሎዬ ፡ በምሕረትህ ፡ ነው (Weloyie Bemehereteh) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:19
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ጣል ፡ አደረኩት ፡ ሁሉን ፡ በአንተ ፡ ላይ
ሁሉ ፡ የሚያምረው ፡ በአንተ ፡ ሆኖ ፡ ሳይ (፪x)
ጭንቀቴን ፡ ወዴያ ፡ ጥያለሁ ፡ ተጨንቄ ፡ ምን ፡ እጨምራለሁ
ሀሳቤን ፡ ወዲያ ፡ ጥያለሁ ፡ አስቤ ፡ ምን ፡ እጨምራለሁ (፪x)

ሰው ፡ በልቡ ፡ ብዙ ፡ ሀሳብ ፡ አለው
የሚሆነው ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ነው
ሰው ፡ በልቡ ፡ ብዙ ፡ ሀሳብ ፡ አለው
የሚፀናው ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ነው

ነገን ፡ ስለማላውቀው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ እያየሁ ፡ አንተን ፡ አከብርሃለሁ
ነገን ፡ ስለማላውቀው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
መሽቶ ፡ ሲነጋልኝ ፡ ማመስገን ፡ ነው ፡ ያለብኝ

ሰው ፡ በልቡ ፡ ብዙ ፡ ሃሳብ ፡ አለው
የሚሆነው ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ነው
ሰው ፡ በልቡ ፡ ብዙ ፡ ሃሳብ ፡ አለው
የሚፀናው ፡ ግን ፡ አንተ ፡ ያልከው ፡ ነው

ነገን ፡ ስለማላውቀው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
ሲመሽ ፡ ሲነጋ ፡ እያየሁ ፡ አንተን ፡ አከብርሃለሁ
ነገን ፡ ስለማላውቀው ፡ ለምን ፡ እጨነቃለሁ
መሽቶ ፡ ሲነጋልኝ ፡ ማመስገን ፡ ነው ፡ ያለብኝ

በሬን ፡ እኔ ፡ ጠብቄው ፡ ከምን ፡ አመልጣለሁ
የአንተ ፡ ጥበቃ ፡ ነው ፡ ከክፉ ፡ የሚያስጥለው (፪x)

ውሎዬ ፡ በምህረትህ ፡ ነው
አዳሬ ፡ በቸርነትህ ፡ ነው (፪x)

እኔ ፡ የኔ ፡ የምለው ፡ እስኪ ፡ ምን ፡ አለ ፡ አለኝ
ዛሬም ፡ ነገም ፡ አንተ ፡ አስተማማኝ (፪x)

ውሎዬ ፡ በምህረትህ ፡ ነው ፡ አሃሃ
አዳሬ ፡ በቸርነትህ ፡ ነው ፡ ኦሆሆ (፬x)