ዋናዬ (Wanayie) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 5:58
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ኢየሱስ ፡ የግል ፡ ነው ፡ የግል ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የግሌ ፡ ነው ፡ አየደል ፡ የጋራ
አልናጠቀውም ፡ ከማንም ፡ ጋራ

ኢየሱስ ፡ የግል ፡ ነው ፡ የግል ፡ ነው
ኢየሱስ ፡ የግልሌ ፡ ነው ፡ አየደል ፡ የጋራ
አልደራደርም ፡ ከማንም ፡ ጋራ

አዝ፦ ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ትርፍ ፡ ነው
ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ ትርፍም ፡ የለም (፪x)
 
በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ
በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ (፪x)

ጠላቴ ፡ ሊያጓጓኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ቢያሳየኝ
ብኩርናዬን ፡ አልሽጥም ፡ የምስር ፡ ወጥ ፡ ይቅርብኝ
ከዔሳው ፡ ተምሬያለሁ ፡ ለምንም ፡ ሆኛለሁኝ

ጠላቴ ፡ ሊያጓጓኝ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ቢያሳየኝ
ኢየሱስ ፡ አልሽጥም ፡ ሰላሳ ፡ ብር ፡ ይቅርብኝ
ከይሁዳ ፡ ተምርያለሁ ፡ ለምንም ፡ ሆኛለሁኝ

አዝ፦ ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላው ፡ ሁሉ ፡ ትርፍ ፡ ነው
ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ ትርፍም ፡ የለም
ዋናዬ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መኖር ፡ እንኳን ፡ ትርፍ ፡ ነው
ዋናዬን ፡ አላስነካም ፡ ካለ ፡ እሱ ፡ መኖር ፡ የለም
 
በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ
በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የማገኘው ፡ ይቅርብኝ
በኢየሱስ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የሚሰጡኝ ፡ ይቅርብኝ
በጌታ ፡ ከሚመጡብኝ ፡ የሚሰጡኝ ፡ ይቅርብኝ

እሳቱ ፡ እጥፍ ፡ ቢነድም ፡ ለምስሉ ፡ አልሰግድም
እግዚአብሔር ፡ አምላኬ ፡ ነው ፡ አምኜው ፡ ነው ፡ ብሞትም
ሊገለጥ ፡ ካለው ፡ ክብር ፡ ሳስተያየው ፡ አይቆጭም

ለምን ፡ አንደመረጠኝ ፡ ይህንን ፡ አሰምራለሁ
ከሁሉም ፡ አስቀድሜ ፡ ጥሪዬን ፡ አከብራለሁ
የእምነት ፡ አባቶቼን ፡ ያለፉትን ፡ እያየሁ

እርሱን ፡ ለማክበር ፡ ለርሱ ፡ ለመኖር
እሽቀዳደማለሁ ፡ እሽቀዳደማለሁ (፫x)
እሽቀዳደማለሁ ፡ እሽቀዳደማለሁ

ከእንግዲህ ፡ እልደለል ፡ ለጊዜያዊ ፡ ነገር
እግዚአብሔር ፡ ያሰበልኝ ፡ የዘላለም ፡ ቁም ፡ ነገር
ከዚህ ፡ አይበልጥብኝም ፡ የቀረው ፡ ሁሉ ፡ ቢቀር

አወዳድሬ ፡ ይሻለኛል ፡ ብዬ ፡ እንዳልናገር
የእኔ ፡ ኢየሱስ ፡ ከምንም ፡ ጋር ፡ አይወዳደር
አስተያይቼ ፡ ይሻለኛል ፡ ብዬ ፡ እንዳልናገር
የእኔ ፡ እግዚአብሔር ፡ ከነጭራሹ ፡ አይወዳደር

ጭክን ፡ አድርጌ ፡ ቆርቻለሁ ፡ ለኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ እኖራለሁ
አልመለስም ፡ ወደኋላ ፡ ጠላቴ ፡ መለከት ፡ ቢነፋ (፪x)