ምትክ ፡ የለህ (Metek Yeleh) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(10)

ርዝመት (Len.): 3:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

እንደ ፡ እናት ፡ ነህ ፡ አልልም
እንደ ፡ አባት ፡ ነህ ፡ አልልም
ምትክ ፡ የለህ ፡ መድህኔ
አንድ ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ ለእኔ (፪x)

አንድ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ጌታ
የለኝም ፡ የማቆመው/የምተካው ፡ በአንተ ፡ ቦታ (፪x)

አንዱ ፡ ሲመጣ ፡ አንዱ ፡ ይሄዳል
በምድር ፡ ያለው ፡ ይቀያየራል
ኢየሱሴ ፡ ካንተ ፡ የተለየ ፡ ሰው
ባንተ ፡ ቦታ ፡ የሚቆምለት ፡ ማነው (፪x)

አንተ ፡ የእኔ ፡ ጌታ
አንተ ፡ ማን ፡ ሊተካ
አንተ ፡ የእኔ ፡ አምላክ
አንተ ፡ የለም ፡ ምትክ (፪x)

ለእኔስ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መሪዬ
የቅርቡ ፡ ተጠሪዬ
የቅርቡ ፡ ተጠሪዬ (፪x)

ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ለእኔ ፡ ማነዉ (፪x)
ከአንተስ ፡ ሌላ ፡ ለእኔስ ፡ ለምኔ (፪x)

ፍቅርህ ፡ ከወይን ፡ ጠጅ ፡ ይልቅ ፡ ይጣፍጣል (፪x)
ፍቅርህ ፡ ከማር ፡ ወለላም ፡ ይመረጣል (፪x)

ይመረጣል ፡ አሃሃ ፡ ይመረጣል (፪x)