መዳኔ (Medanie) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 5:37
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

የትኛውም ፡ ላይ ፡ ልቤን ፡ አልጥልም
ጌታዬን ፡ ከማውቅ ፡ የቱም ፡ አይበልጥም
ሆነልኝ ፡ ከምለው ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
አንዱና ፡ ትልቁ ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

መዳኔ ፡ መዳኔ
መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

ምን ፡ ልይ ፡ ምን ፡ ልፍጠር ፡ ከዚህ ፡ በላይ
አዳነኝ ፡ እኮ ፡ ወርዶ ፡ ከላይ
በምህረቱ ፡ ደግሞ ፡ ሁሌ ፡ ልጄ ፡ ብሎ
አንዴ ፡ ወዶኛል ፡ ላይጠላኝ ፡ ምሎ (፪x)

የትኛውም ፡ ላይ ፡ ልቤን ፡ አልጥልም
ጌታዬን ፡ ከማውቅ ፡ የቱም ፡ አይበልጥም
ሆነልኝ ፡ ከምለው ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
አንዱና ፡ ትልቁ ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

መዳኔ ፡ መዳኔ
መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

ለእኔ ፡ ስላረገው ፡ ያንሳል ፡ ምሥጋና
ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ነው ፡ ያዳነኝና
ለእኔ ፡ ስላረገው ፡ ያንሰዋል ፡ አምልኮ
ከሲዖል ፡ ጣር ፡ ነው ፡ ያዳነኝ ፡ እኮ

ያንሳል ፡ አምልኮ ፡ ከሞት ፡ አፋፍ ፡ ነው ፡ ያዳነኝ ፡ እኮ
ያንሳል ፡ ምስጋና ፡ ከሲዖል ፡ ጣር ፡ ነው ፡ ያዳነኝና

የትኛውም ፡ ላይ ፡ ልቤን ፡ አልጥልም
ጌታዬን ፡ ከማውቅ ፡ የቱም ፡ አይበልጥም
ሆነልኝ ፡ ከምለው ፡ በሕይወት ፡ ዘመኔ
አንዱና ፡ ትልቁ ፡ መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)

መዳኔ ፡ መዳኔ
መዳኔ ፡ ነው ፡ ለእኔ (፪x)