ክብር ፡ ለአንተ (Keber Lante) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 6:41
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ጠዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ ፡ አቀርባለሁ ፡ ምሥጋና (፪x)
ጠዋት ፡ ሳልል ፡ ማታ ፡ እሰዋለሁ ፡ ምሥጋና (፪x)

ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ክበር ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም
እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም
ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ንገሥ ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም
እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም
 
ክበር ፡ ብዬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ይመሽብኛል ፡ ይመሽብኛል
ንገሥ ፡ ብዬ ፡ ሳልጨርስ ፡ ይነጋብኛል ፡ ይነጋብኛል (፪x)

ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ክበር ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም
እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም
ዕለቱን ፡ ሙሉ ፡ ንገስ ፡ ብዬ ፡ ብዬ ፡ አይበቃኝም
እንዲሁማ ፡ በቀላሉ ፡ አይወጣልኝም

ጌታ ፡ ተብሎ ፡ ምን ፡ ይቀጠላል (፪x)
የምጋሥና ፡ ቃል ፡ ሁሉም ፡ አንሶሃል (፪x)
አምላክ ፡ ተብሎ ፡ ምን ፡ ይቀጠላል (፪x)
የዝማሬ ፡ ቃል ፡ ሁሉም ፡ አንሶሃል (፪x)

አንተን ፡ ማምለኪያ (፪x)
እስከዛሬም ፡ አንሷል ፡ ቢጨመርም ፡ ያንሳል
እድሜ ፡ ልክም ፡ ያንልሳል ፡ ዘላለምም ፡ ያንሳል (፪x)

ግን ፡ ያለኝን ፡ አልቆጥብም
ያንሳል ፡ ብዬ ፡ አላቆምም (፪x)

ዳር ፡ ዳር ፡ አልልም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን
አገባለሁ ፡ ምስጋናው ፡ መሃል (፪x)
ዳር ፡ ዳር ፡ አልልም ፡ አንተን ፡ ለማመስገን
አገባለሁ ፡ አምልኮ ፡ መሃል ፡ እገባለሁ ፡ ዝማሬው ፡ መሃል

ማልችለው ፡ አለማምለክ ፡ ነው ፡ ምያቅተኝ ፡ አለማምለክ ፡ ነው
አምልኮ ፡ አውቅበታለሁ ፡ እንዲያውም ፡ አሳምራለሁ (፪x)

እኔ ፡ ምያቅተኝ ፡ እኔ ፡ የማልችለው
አለማመስገን ፡ አለማምለክ ፡ ነው (፪x)

ጌታ (፲፪x)

ክብር ፡ ለአንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል (፪x)
ክበር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይገባል (፪x)

ከትላንት ፡ ይልቅ ፡ ዛሬ ፡ አንተን ፡ ላከብር
ተነሳስቻለሁ ፡ ተነሳስቻለሁ (፪x)

ክብር ፡ ለአንተ ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይሰጣል (፪x)
ክበር ፡ ለአንተ ፡ ነው ፡ እንጂ ፡ ለማን ፡ ይገባል (፪x)

የአንተን ፡ ምሥጋና ፡ ለማንም ፡ አልሰዋም (፪x)
የአንተን ፡ ክብር ፡ ለማንም ፡ አልስጠም (፪x)