ጌታ አሰራሩ (Gieta Aseraru) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)

ርዝመት (Len.): 4:38
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
ምን ፡ ትሰራለህስ ፡ ማነው ፡ የሚለው (፪x)
ጌታ ፡ አሰራሩ ፡ ልዩ ፡ ልዩ ፡ ነው (፪x)
ምን ፡ ታደርጋለህስ ፡ ማነው ፡ የሚለው (፪x)

እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ
አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ

ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ለምን ፡ እሰጋለሁኝ
ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ለምን ፡ አስባለሁ
ለእኔም ፡ እርሱ ፡ ካለልኝ ፡ ማመስገን ፡ ነው ፡ ያለብኝ

ማንም ፡ ከርሱ ፡ ጋራ ፡ ቢሟገትም
ከሺህ ፡ ነገር ፡ እንዱን ፡ አይመልስም
እንዲህና ፡ እንደዚያ ፡ ማን ፡ ይለዋል
አደራረጉ ፡ ግን ፡ አፍ ፡ ያስይዛል

እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ
አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ

ማንንም ፡ አይፈልግ ፡ አስተማሪ
ሁልን ፡ የሚያደርገው ፡ ያላማካሪ
ብቻውን ፡ ተዓምር ፡ ድንቅ ፡ ይሰራል
በዛ ፡ ሲጠበቅ ፡ በዚህ ፡ ይመጣል

አማካሪ ፡ የሌለው ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ
አስተማሪ ፡ የሌለው ፡ መሪ ፡ የእኔ ፡ ጌታ (፪x)

ይሄኛው ፡ ልክ ፡ አይደለም ፡ አስተካክለው ፡ ይህንን ፡ አይባልም
እኔ ፡ አሳይሃለሁ ፡ በዚህ ፡ መንገድ ፡ ሂድልኝ ፡ አይባልም (፪x)

አይባልም (፬x)

እግዚአብሔር ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚሰራውን ፡ የሚያውቅ
አምላኬ ፡ እርሱ ፡ ትልቅ
የሚያደርገውን ፡ የሚያውቅ

ምድርን ፡ አደራ ፡ የሰጠው ፡ ማነው
ዓለምን ፡ ያዝልኝ ፡ ያለው ፡ ማነው
አገዛዝን ፡ ያስተማረው ፡ ማነው (፪x)

ሁሉ ፡ የርሱ ፡ አይደለም ፡ ወይ ፡ አይደል ፡ ወይ
የለበትም ፡ አስተዳዳሪ ፡ የበላይ (፪x)

አማካሪ ፡ የሌለው ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ ኢየሱስ
አስተማሪ ፡ የሌለው ፡ መሪ ፡ የእኔ ፡ ጌታ