ደጄን ፡ ዘግቼ (Dejien Zegechie) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(2)

ርዝመት (Len.): 6:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

ደጃፌን ፡ ዘግቼ ፡ ስልህ ፡ አንተ ፡ ትሰማኛለህ (፪x)
በስውር ፡ የነገርኩህን ፡ በግልጽ ፡ ትቀፍለኛለህ (፪x)

እገባለሁ ፡ በሬን ፡ እዘጋለሁ
ልቤን ፡ ደግሞ ፡ ላንተ ፡ አሳይሃለሁ (፪x)

ሚረዳኝ ፡ የሚረዳኝ ፡ ነው (፪x)
ለኢየሱስ ፡ ነገሬን ፡ ለሚያውቀው
ልግባና ፡ የልቤን ፡ ላዋየው

ሚረዳኝ ፡ የሚረዳኝ ፡ ነው (፪x)
ለኢየሱስ ፡ ነገሬን ፡ ለሚያውቀው
የልቤን ፡ ነግሬው ፡ አልፋለሁ

ወደ ፡ እልፍኜ ፡ ገብቼ
በሬን ፡ ደግሞ ፡ ዘግቼ
የልቤን ፡ ለአንተ ፡ ለአንተ ፡ አዋያለሁ
ለሰው ፡ ባወራው ፡ ምን አገኛለሁ
የልቤን ፡ ለአንተ ፡ ለአንተ ፡ አዋያለሁ
ለሰው ፡ ባወራው ፡ ምን ፡ አገኛለሁ (፪x)

እገባለሁ ፡ በሬን ፡ እዘጋለሁ
ልቤን ፡ ደግሞ ፡ ለአንተ ፡ አሳይሃለሁ (፪x)

ትካዜዬን ፡ በአንተ ፡ ላይ ፡ እጥላልሁ
የምትደግፍ ፡ አንተን ፡ ስላየሁ (፪x)

ለሰው ፡ አላወራም ፡ ትርፉ ፡ መባከን ፡ ነው
የልብ ፡ የሚረዳ ፡ ጌታ ፡ እንዳንተ ፡ ማነው (፪x)

ከአንተ ፡ በላይ ፡ ወዳጅ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ረዳት ፡ እኮ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ተስፋ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ረዳት ፡ እኮ ፡ ማን ፡ አለ

እግዚአብሔር ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)
ጌታዬ ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም
 
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ወዳጅ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ረዳት ፡ እኮ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ተስፋ ፡ ማን ፡ አለ
ከአንተ ፡ በላይ ፡ ረዳት ፡ እኮ ፡ ማን ፡ አለ

እግዚአብሔር ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም (፪x)
አምላኬ ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም
እግዚአብሔር ፡ እንዳንተ ፡ ማንም ፡ የለም