From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ትኩር ፡ ብዬ ፡ ትክ ፡ ብዬ
አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ (፪x)
አይሃለሁ (፪x)
እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x)
ግራ ፡ ገብቶኝ ፡ ሲጨንቀኝ ፡ ሲጠበኝ
ኑሮ ፡ ትክት ፡ ሲለኝ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ
መሄድ ፡ አቅቶኝ ፡ ስወድቅ ፡ ስነሳ
ጉልበቴም ፡ ሲላላ ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ
ዓይኖቼን ፡ ቀና ፡ አርጌ ፡ ያልከኝን ፡ አስታውሳለሁ
መከራዬንም ፡ ሃዘኔንም ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ እረሳዋለሁ (፪x)
እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x)
መድኃኒቴ ፡ የልቤ ፡ ወዳጅ
አንተ ፡ አትጥልምና ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ
አንዴ ፡ መለስ ፡ አንዴ ፡ ደግሞ ፡ ዞር
አያውቅህምና ፡ አንተን ፡ ብቻ ፡ አያለሁ
ደመና ፡ አይቼ ፡ አይደለም ፡ ጌታዬ ፡ ክበር ፡ የምልህ
በተስፋዬ ፡ ላይ ፡ ቆማለሁ ፡ በምድረ ፡ በዳ ፡ አይሃለሁ (፪x)
እዛ ፡ ጋ ፡ አለው ፡ ዋጋ (፬x)
|