አመለጥን (Ameleten) - ቤተልሔም ፡ ተዘራ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
ቤተልሔም ፡ ተዘራ
(Bethlehem Tezera)

Bethlehem Tezera 1.jpg


(1)

አቤት ፡ አምላኬ
(Abiet Amlakie)

ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 4:43
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የቤተልሔም ፡ ተዘራ ፡ አልበሞች
(Albums by Bethlehem Tezera)

እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ያደረገልን (፪x)
ሳንጠፋ ፡ ቀኑ ፡ ሳይጨልም ፡ ደረሰልን (፪x)
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ያደረገልን (፪x)
ሳንጠፋ ፡ ሳይመሽብን ፡ ደረሰልን (፪x)

ወጥመዱ ፡ ተሰባበረ ፡ እኛም ፡ አመለጥን (፪x)
አመለጥን (፬x)

አይቶ ፡ ልቡ ፡ አልችል ፡ ሲለው ፡ አንድያ ፡ ልጁን ፡ ሰደደው (፪x)
አይቶ ፡ ልቡ ፡ አልችል ፡ ሲለው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አንድያ ፡ ልጁን ፡ ሰደደው (፪x)
ወዶ ፡ ስለመረጥኝ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አስቀመጠኝ (፪x)
ወዶ ፡ ስለመረጥኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አስቀመጠኝ (፪x)

ተናጠቀልኝ ፡ ጠላቴን ፡ ተበቀለልኝ (፪x)
ተናጠቀልን ፡ ጠላትን ፡ ተበቀለልን (፪x)
አመለጥን (፬x)
 
የእግዚአብሔር ፡ ምሕረቱ ፡ ስፋቱ ፡ ጥልቀቱ (፪x)
የጌታዬ ፡ ቸርነቱ ብዛቱ ፡ ጥልቀቱ (፪x)
አይደረስበትም (፬x)

አንድያ ፡ ሆኖ ፡ ከሰማያት ፡ መጣ
በኩር ፡ ሆኖ ፡ ወደሰማይ ፡ ገባ
ወንድሞቹን ፡ አስከትሎ ፡ ኋላ

አንድያ ፡ ሆኖ ፡ ከአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ወጣ
በኩር ፡ ሆኖ ፡ ወደአባቱ ፡ ገባ
እኛን ፡ እኛን ፡ አስከትሎ ፡ ኋላ

ጠላቴ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ልፋቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው
እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ
ጠላቴ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ እሩጫው ፡ ከንቱ ፡ ነው

እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ

እኔ ፡ እንደሁ ፡ በጌታ ፡ ካመለጥኩ ፡ ቆየሁ
እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ

አመለጥቁኝ (፮x)