ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሤ (Yehie New Negussie) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(1)

ርዝመት (Len.): 7:34
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ሰው ፡ ያልቻለውን ፡ የሚችለው ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የተዘጋውን ፡ ማህተም ፡ የፈታ ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ
እልፍ ፡ ኣላፋት ፡ ቅዱስ ፡ እያሉ ፡ ሚሰግዱለት
ግርማዊነቱ ፡ ህያው ፡ ንጉስ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ወንበሩ ፡ በሰው ፡ የተደፈረ
ግርማዊ ፡ አይባል ፡ ሞቶ ፡ የቀረ
የእውነት ፡ ግርማዊ ፡ አንድ ፡ ንጉስ
ሞትን ፡ ያሸነፈ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ

ከሞት ፡ ተነሳ (ኢየሱስ) (፪x)
መቃብሩን (ኢየሱስ) ፡ ባዶ ፡ አደረገው (ኢየሱስ)
የይሁዳ ፡ ነገድ (ኢየሱስ) ፡ ሞአ ፡ አንበሳው (ኢየሱስ)
አንበሳው ኢየሱስ(፬x)

ከጥንት ፡ ጀምሮ ፡ ያለ ፡ የነበረ
ዙፋኑ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ ከቶ ፡ ያልተደፈረ
ጉልበት ፡ ያለው ፡ ሁሉ ፡ ሚንብረከክለት
አጋንንት ፡ ለስሙ ፡ ሚንቀጠቀጡለት
እርሱ ፡ የዘጋውን ፡ የሚከፍት ፡ የለ
የከፈተውን ፡ ሚዘጋ ፡ የለ
በሰማይ ፡ በምድር ፡ የሌለው ፡ አቻ
ንጉሰ ፡ ነገስት ፡ ኢየሱስ ፡ ብቻ

ፊቱ ፡ እንደ ፡ ፀሐይ (ኢየሱስ) ፡ የሚያበራ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ከበረዶ ፡ ይልቅ (ኢየሱስ) ፡ ጸጉሩ ፡ ነጭ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ዓይኖቹ ፡ እንደሳት (ኢየሱስ) ፡ ነበልባል ፡ ናቸው (ኢየሱስ)
እንደ ፡ ብዙ ፡ ውሆች (ኢየሱስ) ፡ ድምጹ ፡ አስፈሪ ፡ ነው (ኢየሱስ)
ዮሐንስ ፡ አለ ፡ (ኢየሱስ) ፡ በክብር ፡ ቢያየው ፡ (ኢየሱስ)
ፊቱ ፡ ወደኩኝ (ኢየሱስ) ፡ እንደ ፡ ሞተ ፡ ሰው (ኢየሱስ)

ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፪x)
እንዲህ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፪x)
አንበሳው (ኢየሱስ) (፪x)
ይገባዋል (ኢየሱስ)

ንጉስ ፡ መባል ፡ የተገባው ዝጉን ፡ ማህተም ፡ የፈታው
ለሌላ ፡ አንሰጥም ፡ ክብሩን ሞትና ፡ ትንሳኤውን
መባል ፡ ያለበት ፡ ሞአንበሳ ሞትን ፡ ድል ፡ አድርጎ ፡ ለተነሳ
ሰማይ ፡ ያረገ ፡ በደመና ዳግም ፡ ሚመጣ ፡ እንደገና

ይሄ ፡ ነው ፡ ንጉሥ (ኢየሱስ) (፬x)
አንበሳው ፡ ኢየሱስ (፪x)
ኢየሱስ

የደስታዬን ፡ ዕልልታ (፪x) ፡ ንጉሥ ፡ ለሆነው ፡ ፡ ጌታ
የደስታዬን ፡ ዕልልታ (፪x) ፡ አስማለሁ ፡ ለጌታ
የደስታዬን ፡ ጩኸት (፪x) ፡ ለንጉሠ ፡ ነገሥት
የደስታዬን ፡ ጩኸት (፪x) ፡ እስቲ ፡ ልጩኽለት

መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ እስቲ ፡ ናልኝ ፡ ኢየሱስን ፡ አክብርልኝ
የውስጤ ፡ ጥማት ፡ መሻቴ ፡ ወልድ ፡ ሲከብር ፡ በሕይወቴ
አምልኮ ፡ የሚያምርብኝ ፡ ጎኔ ፡ ስትቆምልኝ
በመውጣት ፡ መግባቴ ፡ ላይ ፡ ንጉሳችን ፡ ሁን ፡ የበላይ
ሁንልኝ ፡ የበላይ (፬x)
ሁንልኝ ፡ የበላይ (፬x)


የበላይ (፬x) ፡ የበላይ (፬x)
የበላይ
የበላይ ፡ እህህህም ፡ የበላይ