መዳኛ (Medagna) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(6)

ርዝመት (Len.): 6:32
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አዝመዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)

ህልመኛው ፡ ተሽጦ ፡ ለግብፃዊ ፡ ቤት
አገልጋይ ፡ እንዲሆን ፡ ለረጅም ፡ ዓመት (፪x)
ሲመላለስ ፡ ሳለ ፡ በታማኝነት
በሀሰት ፡ ወንጅለው ፡ ከወይኒ ፡ ጣሉት (፪x)

ለመልካም ፡ ሆነለት ፡ አንተን ፡ በማክበሩ
ህልሙ ፡ እውን ፡ ሆነ ፡ ወጣ ፡ በመምበሩ (፪x)
ሰው ፡ ሳያይ ፡ በጓዳ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ፈሪ
መሆኑ ፡ አይቀርም ፡ ተፅዕኖ ፡ ፈጣሪ (፪x)

የተጣለን ፡ ምታነሳ ፡ ለምስኪኑ ፡ ምትሳሳ
የታሰረን ፡ የምትፈታ ፡ የደህንነት ፡ ጌታ (፪x)

አዝመዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)

መከራው ፡ ስቃዩ ፡ ሲያልፍ ፡ በሕይወቴ
ከጐኔ ፡ አልተለየህ ፡ ኢየሱስ ፡ ረዳቴ ፡ ኢየሱስ ፡ አባቴ
እንዳያልፍ ፡ አለፈ ፡ ያ ፡ ሁሉ ፡ መከራ
ሃሩር ፡ ተሻገርኩኝ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋራ ፡ ከኢየሱሴ ፡ ጋራ

የበረሃው ፡ ፀሐይ ፡ እንዳያቃጥለኝ
ደመናን ፡ አዞልኝ ፡ ጥላ ፡ አደረገልኝ (፪x)
እባብ ፡ እና ፡ ጊንጡ ፡ ነድፎ ፡ እንዳያስቀረኝ
ከፊቴ ፡ እየወጣ ፡ እረጋገጠልኝ (፪x)

አዝመዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ (፪x)
ለተረሳው ፡ ሰው ፡ ጓደኛ
መዳኛ ፡ ነህ ፡ መዳኛ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)
አሳደከኝ ፡ ከልጅነቴ
አባቴ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፪x)