ሁሉን ፡ ቀድሜዋለሁ (Hulun Qedemiewalehu) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(4)

ርዝመት (Len.): 7:30
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ

ጥበበኛዋ ፡ ሴት ፡ ቀዝቃዛውን ፡ ክረምት
ሩቅ ፡ አይታ ፡ ልብሷን ፡ ሰፋች ፡ መከራውን ፡ ቀደመች
እኔም ፡ እንደ ፡ እሷ ፡ ሁሉን ፡ ቀድምያለሁ
በእየሱስ ፡ ተደስቻለሁ (፪x)
ሃዘንን ፡ ቀድሜዋለው ፡ ጭንቀትን ፡ ቀድሜዋለው
ተድላን ፡ ቀድሜዋለው ፡ ስኬትን ፡ ቀድሜዋለው

የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ

የተቀደመ ፡ ነው ፡ የቀረው ፡ ዘመኔ
የዘላለም ፡ ደስታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖኝ ፡ ለእኔ
ቀድሜ ፡ ተደስቻለው (፪x)
በኢየሱስ ፡ ተደስቻለው (፪x)

እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
አይቋረጥም ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ

የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ (፪x)
ነገር ፡ ቢሞላ ፡ ነገር ፡ ባይሞላ
የሰላሜ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ

ደስታ ፡ እና ፡ ሃዘኔ ፡ እኩያ ፡ ነበሩ
በልኬት ፡ ቁመና ፡ የሚፎካከሩ
ኢየሱስ ፡ ግን ፡ የሰጠኝ ፡ ደስታ
አይስተካከል ፡ ከሁኔታ
አባቴ ፡ የስጠኝ ፡ ደስታ
አይስተካከል ፡ ከሁኔታ

እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ
እንደ ፡ ወንዝ ፡ ነው ፡ ሰላሜ (፫x)
ይፍለቀለቃል ፡ ከውስጤ

የደስታዬ ፡ ምንጭ ፡ አንተ ፡ ነህ
አንተ ፡ ነህ