ጌታን ፡ አገኘሁ (Gietan Agegnehu) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(5)

ርዝመት (Len.): 4:55
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ተጭኖብኝ ፡ የማልችለውን
የሞት ፡ ፍርሀት ፡ አርጎኝ ፡ ምስኪን
መች ፡ አገዝኝ ፡ የእኔነት ፡ ካባዬ
አልቆ ፡ ነበር ፡ የመኖር ፡ ተስፋዬ
ግን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ
ይታደጋል ፡ ያድናል ፡ ሲሉኝ
በቅንነት ፡ እጄን ፡ አነሳሁኝ
የዛች ፡ ለት ፡ ጌታን ፡ አገኘሁኝ

አዲስ ፡ ነገር ፡ የዛች ፡ ለት ፡ ሆነ (፪x)
በመንፈሴ ፡ ሰላም ፡ ሰፈነ (፪x)
አፈሰሰው ፡ በልቤ ፡ ደስታ (፪x)
መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ የሰላም ፡ ጌታ (፪x)

በአገር ፡ በሰፈሩ ፡ እታማ ፡ ጀመረ
የእናት ፡ እና ፡ የአባቱን ፡ ሃይማኖት ፡ ቀየረ
ይህን ፡ ያንን ፡ ብለው ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ ተነሱ
እኔ ፡ የቀመስኩትን ፡ ምነው ፡ በቀመሱ

ኢየሱስ ፡ ብቸኛ ፡ አማራጭ ፡ የሌለው
ወደ ፡ ሰማይ ፡ መግብያ ፡ ብቸኛ ፡ መንገድ ፡ ነው
ያዳነኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የሞተልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የተወጋልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

መዘበቻ ፡ አርጓት ፡ ነፍሴን ፡ ሰይጣን ፡ ክፉ ፡ አይራራ ፡ አያዝን
ከሱ ፡ ለማምለጥ ፡ ብዙ ፡ ጣርኩኝ ፡ ግን ፡ አልቻልኩኝ
በዚህ ፡ ሁኔታ ፡ ወንጌል ፡ ሰማሁኝ ፡ እየሱስን ፡ ተገናኘሁኝ
ሰው ፡ መሆኔን ፡ የወደድኩት ፡ ያየሁት ፡ ለት

የልጅነትን ፡ ሥልጣንን ፡ ሰጠኝ ፡ ሥልጣን ፡ ያሳደደኝን ፡ አሳደድኩኝ ፡ አሳደድኩኝ
የበቀል ፡ ቅባት ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ ፡ እራሴን ፡ ቀባኝ
ያስጨነቀኝን ፡ አስጨነኩኝ ፡ አስጨነኩኝ

እናንተ ፡ ደካሞች ፡ ሸክማቹህ ፡ ከባድ
ወደ ፡ እኔ ፡ ኑ ፡ ያለ ፡ ይሄ ፡ ሰውን ፡ ወዳጅ
ያሳረፈኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ሰው ፡ ያደረገኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ያከበረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ያዘመረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ዋጋ ፡ ከፍሎ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
በደም ፡ ገዛኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
ከጻድቃን ፡ ጋር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው
የቀላቀለኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው