ባለውለታዬ (Baleweletayie) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(8)

ርዝመት (Len.): 6:40
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ወረቀት ፡ ብዕሬን ፡ አገናኘሁኝ
ስለጌታ ፡ ውለታ ፡ መጻፍ ፡ አሰኘኝ
የትኛውን ፡ ጽፌ ፡ የቱን ፡ ልተወው
የምለውን ፡ ባጣ ፡ እንዲህ ፡ ልበለው ፡ ልበለው

ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x)

ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው
የእግዚአብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል
እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል

ታሪክ ፡ የሌለውን ፡ ባለታሪክ
ጠላት ፡ የሆንኩት ፡ ወዳጅ ፡ አረክ
አሳዳጅ ፡ የሆንኩትን ፡ ነካኽኝና
በቅዱሳኑ ፡ ፊት ፡ አቆምከኝና

ዘምር ፡ አልከኝ (፬x)

በስንኝ ፡ ቋጠሮ ፡ ችዪ ፡ ላልሰንቅ
ጠልቄ ፡ ባስብም ፡ አቅሜ ፡ እስኪያልቅ
አወይ ፡ በትንሿ ፡ በዚች ፡ ወረቀት
ጭሬ ፡ አልጨርሰው ፡ የሱን ፡ ሰጪነት ፡ ለጋስነት

መካኒቱ ፡ ሰባት ፡ ወለደች
ሳራም ፡ በእርጅና ፡ ጸነሰች
ሙሴን ፡ በጥበብ ፡ አሳደገ
ምስኪኑን ፡ ዳዊት ፡ ንጉሥ ፡ አደረገ

እንደዚህ ፡ ነው ፡ የኢየሱስ ፡ ስራ
አይጨረስ ፡ ሁሌም ፡ ቢወራ
እኔም ፡ አለኝ ፡ የምለው
አግኝቶኛል ፡ ውለታው

ባለውለታዬ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፬x)

ውለታ ፡ አለብኝ ፡ የማልመልሰው
የእግዛብሄር ፡ ልጅ ፡ ለእኔ ፡ የሰራው
ስለ ፡ ኢየሱስ ፡ ሰፊ ፡ ጊዜ ፡ ያሻኛል
እንኳን ፡ ቀኑ ፡ ዘላለም ፡ ያንሰኛል

ብዙ ፡ ነው ፡ የሱ ፡ ውለታ
ሳስበው ፡ ጥዋት ፡ እና ፡ ማታ
ግርም ፡ ይለኛል ፡ ድንቅ ፡ ይለኛል ፡ ቃላት ፡ ያጥረኛል
በምን ፡ ቋንቋ ፡ ነው ፡ በምን ፡ አንደበት
የምገልጸው ፡ የሱን ፡ በጐነት (፪x)