አቤት ፡ ደግነት (Abiet Degenet) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Bereket Tesfaye 2.jpg


(2)

ታይልኝ
(Tayelegn)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፰ (2016)
ቁጥር (Track):

(3)

ርዝመት (Len.): 5:09
ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

እውነትነቱን ፡ በመስቀል ፡ ላይ
መቶ ፡ አለቃው ፡ ጌታዬን ፡ ቢያይ
ተንበረከከ ፡ ሰገደለት
ነካው ፡ የጌታ ፡ ቅንነት
እንኳን ፡ አሁን ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ብሎ
አሸንፎአል ፡ ተንጠልጥሎ
ሳያስፈራራ ፡ ሰው ፡ አንበርካኪ
እንደእርሱ ፡ የለም ፡ ፍቅር ፡ ሰባኪ

አቤት ፡ ደግነት ፡ ቸርነቱ
ለሰው ፡ ያሳየው ፡ ምህረቱ (፮x)

ፍቅር ፡ ምህረቱን ፡ የቀመሱቱ
ውበቱን ፡ ያዩ ፡ ሐዋሪያቱ
ስለእርሱ ፡ ኖረው ፡ መረጡ ፡ ሞት
ለፍቅሩ ፡ ሆኑ ፡ ሰማዕታት

ተነክተው ፡ በምህረቱ
ተነክተው ፡ በቸርነቱ
ነክቶአቸው ፡ ገርነቱ
ነክቶአቸው ፡ የዋህነቱ

የቱ ፡ ጀግና ፡ ነው ፡ እጁን ፡ ያልሰጠ
የሱስን ፡ አይቶ ፡ ያልደነገጠ
ልከተልህ ፡ ያላለ ፡ ማነው
የኢየሱስ ፡ ፍቅር ፡ አሸናፊ ፡ ነው

ከጫፍ ፡ ጫፍ ፡ ስንቱን ፡ ማረከ
በፍቅሩ ፡ አንበረከከ
ምን ፡ ዓይነት ፡ ፍቅር ፡ ነው ፡ እንጃ
ወደደንው/ሰገድን ፡ያለ፡ ጠመንጃ (፪x)

አቤት ፡ትህትና ፡አይ ፡ቅንነት
ሰውን፡ ያስተማረ ፡ኖሮ ፡በሕይወት
የሚሸጠውን፡ እግር ፡ ያጠበ
ሩህሩህ ነው ጌታ፡ ፍቅር ፡ያነገበ

ይህንን ፡ ጌታ ፡ የምትወዱት
አስቲ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ኢየሱስን ፡ እንዲህ ፡ በሉት (፪x)
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ እንዳንተ ፡ ያለ
እንዳንተ ፡ ያለ ፡ ኧረ ፡ ማን ፡ አለ (፬x)