የቅርቤ (yekerbe) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፲ ፩ (11)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ከሲዖል መውጣቴ ይበቃኝ ነበረ
በዚያ አላበቃም ፍቅሩ ጨመረ
ቀረበኝ አልሆንኩም ብቸኛ
አምላኬ ልክ እንደ ጓደኛ
ሳይዘው ሳይገድበው ትልቅነቱ
አብሮኝ ነው ኢየሱስ ትሁቱ
የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ (2X)
ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ
የቅርቤ ልበልህ የቅርቤ
 ከእስትንፋሴ ይልቅ ይልቅ የቅርቤ ነህ
  ፊትህን ተርቤ መቼ መቼ አጣሁህ
  የሆድ የውስጤን ታውቀው የለም ወይ ሳልተነፍስ
  ውዴ ኢየሱስ
ሰው ሚያውቀው ጉብዝናዬን
መቼ አየ ገመናዬን
ሸፍነኸው ጉድለቴን
ሚታየው ግን ሙላቴ
  የቅርቤ...
ዞር ብዬ ወደ ኋላ መንገዴን ሳይ
የአንተ እንጂ የእኔ ኮቴ አይታይ
አባጣ ጎርባጣውን እኔ መውጣቴ
ይዘኸኝ ልክ እንደ እናቴ
ምንም ባሳዝንህ በድካሜ
ታግሰኽ አቆምከኝ መድህኔ
  ሰው ሚያውቀው...
በሰዎች መሐል ወይም ለብቻዬ
ድምፁን ያሰማኛል አብሮኝ ነው ጌታዬ
በዚህ ሂድ በዚያ ሂድ እያለኝ
ጠላት የማሰውን አለፍኩኝ
አምላኬ የመከረኝን
ሰምቼው አለፍኩኝ ስንቱን
  የቅርቤ...
  ሰው ሚያውቀው...
  የቅርቤ...