ለመልካም ሆነልኝ (lemelkam honelegn) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(10)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ለካ ይታለፋል ማይታለፈው
ከልኩ አያልፍም የሰው ፈተናው
ምጠፋ መስሎኝ ፈራች እንጂ ነፍሴ
ለካ ያስጨነከኝ ለጥቅሜ ለራሴ
በእሳት እያለፍኩ ስፈተን
ወርቅ አደረገው ህይወቴን
  ጌታ ሆይ አሁን ተማርኩ ተስተካከልኩ
  አመፃን ጥዬ ፅድቅንም ያዝኩ
  ያ ልፍስፍሱ ጠነከረ እንጂ ልቤ
  አላጠፋኝም የጋለው ከአጠገቤ
  ተስማምቶ የኖረ ከአፈር እና ከጭቃ
  እሳት ሲያገኘው ሆነ የክብር ዕቃ
  ጠንክሬ በርትቼ እንድመላለስ
  ልቤን አጀገነው ቅዱሱ መንፈስ
  ቀዝቃዛ ሂወቴ በፈተናው ሞቀ
  እሳቱ ሲነካው ነጠረ ደመቀ
  ዘመኔ እንዲደምቅ እንዲያበራ
  መቼ መሰለኝ የምሰራ
  ልክ እንደ ድንጋይ ተራ የነበረ
  እሳት ሲያገኘው ሆነ የከበረ
  ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ (2X)
  ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ (2X)
  ለመልካም ሆነልኝ ሆነልኝ
  ለመልካም ሆነልኝ ያስጨነከኝ
  ለበጎ ሆነልኝ ሆነልኝ
  ለበጎ ሆነልኝ ያስጨነከኝ
በመከራ ውስጥ መታዘዝን ተማረ
በስጋው ወራት አንተን አከበረ
እኛ ዳንን እንጂ በእርሱ መከራ
ህይወታችን ጣፍጧል በጠጣው መራራ
እሱ ኃያል ሳለ ምስኪን መሰለ
ከአመፀኞች ጋር ተሰቀለ
በጌታ መከራ ስንቶች ዳኑ
አቀረባቸው ወደ ዙፋኑ
  ጌታ ሆይ...