የውሃ በረሐ (Yeweha Bereha) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፲ ፪ (12)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ብዙ ፍጥረት ያለው ባህር ውቅያኖሱ
ለየብስ ሩብ ሰጥቶ ቀሪውን መልበሱ
ላጥፋ ካለ አጥፊ ጡንቻ አለው ፈርጣማ
ካንዱ ጌታ በቀር ማንንም አይሰማ
ጥም አርኪ ይመስላል ግን ለጠማው ደሃ
ውስጡ ስለሌለው ለመጠጥ የሚሆን አንድ ብርጭቆ ውሃ
ሰነፍ መርከበኛ ውቅያኖሱ ዳር
ሚጠጣውን ሰይዝ መጓዝ ቢጀምር
ውሃ መሃል ደርሶ ውሃ ይጠማዋል
ውሃ በረሃ ላይ በውሃ ጥም ይሞታል
አንድ ጉድጓድ አለች በጣም ትንሽዬ
ህፃን ነህ አዋቂ ጨዋ ነህ ዱርዬ
ሳትል ሳታዳላ ሁሉን ታጠጣለች
ይህን ንፁህ ውሃ ታመነጨዋለች
ጠቢቡ ገበሬ እሷ ዳር ይዘራል
ዘሩም ምንጯን ነክቶ ማን ደርቆ ይቀራል
ጌታ ኢየሱስን በዕምነቱ የነካ
ከህይወት ውሃ ምንጭ ጠጥቶ እረካ
ስንት ምስኪነ አለ ሳይተኛ ሚያነጋ
ነፍሱ ምትገረፍ በጥማት አለንጋ
እግዚአብሔር ነፍሱን ነይ ላርካሽ ቢላት
የእግዚአብሔርን ሳይሆን ለነፍሱ ሆዱን ሰማላት
ጌታ በሌለበት በዚያ ባዶ ቦታ
ምኑንም ቢከቱ አይሰጥም እርካታ
ሰማይ እና ምድር ባንዴ ተጠቅልሎ
የኢየሱስን ቦታ አይሞላውም ችሎ
የተከበበ በማይጠጣ
በዓለም ያለ ሰው ኢየሱስን ያጣ
በጀልባ እንደጠፋ ውቅያኖስ ላይ
ኢየሱስ የሌለው ሰው እሱ አይደል ወይ
ተበልቶ ተጠጥቶ የለም እርካታ
ኑሮ ማለት ሃሩር ከሌለው ጌታ
ዳግመኛ አልጠማኝም አንዴ ጠጥቼው
ጎዶሎ የለኝም ውስጤ ሙሉ ነው