መምህሩ (Memheru) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(4)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የሞተን በቃሉ የሚያነሳ
ደግሞም የሚፈውስ......
ሳይታይ ጠባሳ
ምስክር ለሚሻ እኔ አለሁ
በስሙ አምኜ ተፈውሻለሁ
እንኳን ፊቱ ያለሁቱ (እንኳን ስሙን ያመንኩቱ)
ዳኑ ከጀርባ የነኩቱ
ኢየሱስ ብሉ የተጣራ
በልቷል ፈውስን እንደ እንጀራ

       ፈውስን እንደ እንጀራ እንደ እንጀራ (2X)
ሀገር የሚያውቃት ከቤተ መቅደስ ስትመላለስ
ለፈውሷ ሳይሆን አምላኳን ወዳ ቀድማ የምትደርስ
ያሸማቀቃት ያስጎበጣትን ጀርባዋ ላይ
ይዛ ስትገባ ለካ ቀደሟታል ቅኖች የሚያይ

       ቢዳስሳት ጌታዋ
      ተፈወሰ ጀርባዋ
      ወደቀላት ቀንበሩ
      ስለመጣ መምህሩ
            አዳኝ መጥቷል መምህሩ
            ፍቅር መጥቷል መምህሩ
           ንጉስ መጥቷል መምህሩ
           ፈዋሽ መጥቷል መምህሩ

ደከመኝ ሳትል ተመላለሰች
ህመሟን ይዛ እቤቱ መጣች
ልክ እንደ ልማዷ ከምኩራብ ስትደርስ
የዛን ዕለት ሰባኪው መምህሩ ኢየሱስ

      ቢዳስሳት ጌታዋ
      ተፈወሰ ጀርባዋ
      ወደቀላት ቀንበሩ
      ስለመጣ መምህሩ
           አዳኝ መጥቷል መምህሩ
           ፈዋሽ መጥቷል መምህሩ
           ......... መጥቷል መምህሩ
                  ፍቅር መጥቷል መምህሩ (5X)

ልጅቷ ሞታለች አታድክም መምህሩን
ለወላጅ አባቷ ብለው አረዱት መርዶን
አትፍራ ብቻ እመን ሰምቶ አለው ጌታ
እቤታቸው ሄደ ባዛ ለቅሶ ጫጫታ
ተኛች እንጂ መች ሞተች
ቢላት ሳቁ ለቀስተኞች
ጌታ ወደ ውስጥ ገባና
ተነሽ አንቺ ብላቴና
በድኗ ልጅ ተነሳች
የጌታን ድምፅ ሰማች
ሙታን አቤት ሚሉት
ኢየሱስ የዓለም መድሃኒት

        እንኳን ፊቱን የጀርባውን ቀሚስ
        አይተው የለ ወይ የነካው ሲፈወስ
        አልዳነችም ወይ ያቺ ምስኪን
        በዕምነት ብትነካው ቀሚሱን

እንኳንስ ፊቱን ጀርባው መድኃኒት
አምኖ ለነካው የሚሰጥ ሂወት
የሚያገፋፋው አላማኝ መች ታጣ
በዕምነት ለነካች ከጀርባው ኃይል ወጣ

          ፈውስ እንደ እንጀራ.....
          እንኳን ፊቱ ያለሁቱ......

ይህን ወንጌል ያልሰማ እንዲሰማ
አውጃለሁ ከገጠር ከተማ
እንደሚያድን እንደሚታደግ
እሰብካለሁ ስለ እግዚአብሔር በግ
ያድናል የምለው እኔ
አድኖኝ ስላየሁ ባይኔ
ያድናል እኔ ያልኩት
አድኖኝ ስላየሁት

      ያድናል (8X)