ማራናታ (Maranata) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(5)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የመምጣትህ ነገር የመጨረሻው
የነገርከን ትንቢት እየሆነ ነው
ናፍቆቱ አስባለኝ አሜን ማራናታ
ላይህ ጓጉቻለሁ ኢየሱስ የኔ ጌታ
ጌታ ኢየሱስ አትመጣም ወይ
የደማልኝን ጎንህን ልይ
አንተን ለማየት አይኖቼ ሻቱ
ቶሎ ናልኝ ኢየሱስ የናዝሬቱ
ካንተ ጋር ልዋል ካንተ ጋር ልደር
እንደ ዮሐንስ በደረትህ ሥር
ደስታ የምለው ትልቁ እርካታዬ
አንተ ያለህበት ስኖር ነው ጌታዬ
በሌለህበት ከማገኝ ድሎት
ምድረበዳ ላይ ካንተ ጋር ልሰንብት
አንተን የማየት ናፍቆት ገባብኝ
እንደ ጓጓሁኝ መች እቀራለሁኝ

  ከአመፃ ብዛት ፍቅር ቀዘቀዘ
  ሰው ወንድሙን ገሎ መቼ ተወቀሰ
  አመፀኞች በዙ ክፋቱ ጨምሮ
  ተላልፈው ተሰጡ ለማይረባ አዕምሮ
  የድሆች ዳኛ የሁሉ አለቃ
  ና እና ከልክለው ለቅሶአችን ይብቃ
  የእናቶች እምባ ይላል ዋይ ዋይ
  ሩህሩህ ጌታ አትመጣም ወይ
  ቤተ ክርስቲያን ተነሺ እና አብሪ
  ፍቅርን ለጣሉ እንዳትዘምሪ
  የገሃነም ደጅ ለካ ጥላቻ ነው
  ማይቋቋምሽ ሰይፍሽ ፍቅር ሲሆን ነው
  ጦር መሳሪያውን ፍቅር ያደረገ
  ጠላቱን ረቶ ወንድም አደረገ
  የሰው ጠባብ አፍ የሚጎርስ እህል
  ክፉ አንደበት አክሏል ሲዖል

    አትመጣም ወይ ማራናታ
አናርፍም ወይ ማራናታ (2X)

    ና ና ና ና ና ማራናታ (4X)
ሃሳዊ መምህራን ነብያቶች በዙ
ተናገረኝ ባዮች ለገንዘብ የተገዙ
ለታመመው ምስኪን እንግዳ ማረፊያ
በሽታው ሳያንሰው በፀሎት ሰበብ ዝርፊያ
ደምህ ተረግጦ ገንዘብ ገነነ
አንተን ያወቀ ሰው ክፉ ሆነ
ነዋይ ሚያፈቅር ትውልድ ተነሳ
ያረክለትን ምህረት የረሳ
ፈውሱ ለታይታ ለንግድ ቀረበ
በአዳኙ ስም ገንዘብ ተሰበሰበ
ገበያው ደርቶ በወንጌል ሰበብ
ስንቱን ታዘብነው አወይ ጉድ አጀብ
በሰጠው ፀጋ የሆነ ነጋዴ
በፍርድ ቀን የሚል ነው ወይኔ ጉዴ
መምጣቱ አይቀርም የእረኞች አለቃ
ስለበጎቹ የሚራራ ጠንቃቃ

  አትመጣም ወይ...
  ና ና...

ወደ ዓለም ሂዱ ወንጌልን ስበኩ
ነበር የተባልነው መስክሩ ታደጉ
ሰው ግን ካስማ ሰርቶ ወንበሯን ወደደ
መምህር እና ጌታ መባልን ለመደ
ወንጌል እንስራ አንቱታው ቀርቶ
ይሸለም የለ ወይ የሰራ ተግቶ
ከታበይንበት ዙፋናችን
እስኪ እንውረድ ለጌታችን
አላወጣንም አጋንንቶችን
አልፈወስንም ወይ በሽተኞችን
ጌታ በስምህ ብዙ አድርገን
አላውቃችሁም ስለምን አልከን
ከሚሉት ወገን እንዳይሆን ሂወቴ
መብራቴን ላብራ ሳይጎድል ዘይቴ
እስክተመጣልኝ ወይ እስክትወስደኝ
እየጠበኩህ እፀናለሁኝ

  ና ና...