ክብር አለ (Kiber Ale) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(7)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

ሃሌሉያ እያሉ መላዕክት በሙሉ
ኢየሱስ ለሚል ስም ይንበረከካሉ
አይነፃፀርም ከተዋረዱቱ
ስሙ ከፍ ያለ ነው በሰማይ ካሉቱ
ለቆ ከፍ ያለ የተከበረ
በሰማያት ላይ አንድ ስም አለ
ስሙን ሊያከብር ጰራቅሊጦስ
ከሰማይ መጥቷል መንፈስ ቅዱስ
በስሙ ላይ ክብር አለ (3X)
ማዳን አለ ክብር አለ
ፍቅር አለ ክብር አለ
እዚህ ስም ላይ ክብር አለ
ዘይት አለ ክብር አለ
ማዳን አለ ክብር አለ
ቅባት አለ ክብር
የትኛው ተራራ ነው
ስሙ ሲጠራ የሚቆመው
  የትኛው ሸለቆ ነው
ይሄ ስም የማይሞላው
  የትኛው በሽታ ነው
በዚህ ስም ፊት የሚቆመው
  የትኛው ሰይጣን ነው
 ስሙ ሲጠራ የሚቆመው
    በስሙ ላይ ክብር አለ (3X)
    ቅባት አለ ክብር አለ
ማዳን አለ ክብር አለ
    ኢየሱስ ስም ላይ ክብር አለ (7X)
ቅዱስ ስሙን አመልካለሁ ለሌለው እኩያ
አሁንም ክብር ይሁን ለኢየሱስ ስም ሃሌሉያ
  ዕውር ሚያበራ ሽባ ሚተረትር
  ከአብ የተሰጠን የክርስቲያን በትር
  ፃድቅ ሰው ጠርቶት መች ተሸነፈ
  ክፉ የት አገኘዉ እንዳሰፈሰፈ
    እዚህ ስም ላይ ክብር አለ
ፈውስ አለ ክብር አለ
    ታምራት አለ ክብር አለ
ሂወት አለ ክብር አለ
    ድነት አለ ክብር አለ
ከፍታ አለ ክብር አለ
    ክብር አለ (4X)
የኢየሱስ ስም ከስሞች
ሁሉ በላይ ነው በላይ ነው (4X)
እንኳን በምድር መንግስተ ሰማይ
ሁሉ አሻቅቦ ሚያየው ወደላይ
የኢየሱስ ስም የስሞች ማማ
ፃድቅ ጀግኗል ስሙን ሲሰማ
  ክብር አለ (16X)