እሱ ሰው ከበረ (Esu Sew Kebere) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

፲ ፫ (13)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

በለሷን ፍሬዋን የጠበቀ
ይበላል ትግስቱ ያላለቀ
ጌታውን የጠበቀ ሰው
ስፍራዬን አለቅም ያለው
እሱ ሰው ከበረ አሄሄ ጌታን ያከበረ (2X)
      ስምዖን ትጉህ እና ፃድቅ ሰው ነበረ
      አያለው ቅዱሱን እያለ የኖረ
      ሲጠብቅ ቆይቶ ህፃኑን ሲያየው
      እጆቹን አንስቶ እንደዚህ አለዉ
ለህዝቦች ሁሉ መድኃኒት (2X)
የሆነውን እሱን ስላየሁት (2X)
መኖር አልሻም ውሰደኝ በቃ (2X)
በፅድቄ የኖርኩት እሱን ጥበቃ ልጁን ጥበቃ
        ለኔ ስኬት (3X) ጌታን ማየት
        ለኔ ከፍታ (3X) ፊትህ ነው ጌታ
ያርስ የለ ወይ በበጋ ልቡን ጥሎ
ገበሬው አምኖ ይዘንባል ብሎ
በደረቅ መሬት አምኖ ያረሰ
በክረምት እርሻው እረሰረሰ
እኔም እጠብቅሃለው
መውደዴን በዚ አሳይሃለው
አንድ ቀን ዓለም እያየህ
ልትወስደኝ ትመጣልኛለህ
        ለኔ ስኬት...
        ለኔ ከፍታ....
        በለሷን.....
ፍፃሜው ክብር ነው አንተን መጠበቄ
መብራቴን አብርቼ ወገቤን ታጥቄ
እጠብቅሃለሁ እስክትመለስ
ሙሽራው አዳኜ ጌታዬ ኢሱስ
  ፊትህን እንዳይ ተርቤ የለ ወይ እርቦኝ የለ ወይ
  ለጥቂቶች ማዳን ብትዘገይ (2X)
  ጨመረብኝ ፍቅርህ በየለቱ (2X)
  ተናፍቀኃል ኢየሱስ የናዝሬቱ (2X)
           እስክትመጣ እስክትመለስ
            ጠብቅሃለው ውዴ ኢየሱስ
             ጠነከተብኝ ፍቅርህ በረታ
              በቶሎ ናልኝ የህይወቴ ጌታ