አሜን አሜን (Amen Amen) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(9)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አሜን አሜን (16X)
ወንጌል ሲነገረኝ አትንገሩኝ ባይ
ጠንካራ ነበረ ልቤ እንደ ድንጋይ
ግን አንድ ቀን ጭንቀት ወደ ህይወቴ መጣ
ዕውቀት የመሰለኝ ምንም አላመጣ
ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ ልሞክረው ብዬ
በስብከት ሞኝነት አሄ ይሁን አሜን ብዬ
አይቼ ማላውቀው የደስታ ካባ
ህይወቴ ለበሰ ኢየሱስ ሲገባ
ዛሬማ እሞትለታለሁ
ሂድ ቢለኝ ወዴት እሄዳለሁ
እሱ ነው የመጨረሻዬ
አሜን ያልኩት ኢየሱስ ጌታዬ
አስገባሁት አሜን ልቤን ከፍቼ አሜን
ይኸው አለሁ አሜን ድኜ ቀርቼ አሜን
ያስገባሁት አሜን አሜን ብዬ አሜን
መድኃኒት ሆነኝ አሜን ኢየሱስዬ አሜን
    ኢየሱስዬ ውድዬ (4X)
      አሜን አሜን...
እንኳንስ ሊያቀርበኝ ሊገባ ከቤቴ
መጥራት ማይገባኝ ስሙን በአንደበቴ
ጌታ ግን ደግ ነው ምህረት የለበሰ
ለጠፋሁት ልጁ ፍቅርን ደገሰ
ፍርድ ነበረብኝ በሞት የሚያስቀጣ
የገዛ በደሌ ያመጣብኝ ጣጣ
ጌታ ግን ከፈለ የኃጢያቴን ዕዳ
አሜን በማለቴ ነውሬን አፀዳ
በኢየሱስ ህይወት አጊንቻለሁ
ልለየው እንዴት እችላለሁ
እስካይችል ይሄ ትከሻዬ
አይሏል ፍቅሩ በላዬ
አስገባሁት....
ኢየሱስዬ...
አሜን አሜን...
ከሰማይ ወረደ አሜን አሜን ደግሞ
ለእኔ ሞተ አሜን አሜን
ከሙታን ተነሳ አሜን አሜን
በክብር አረገ አሜን አሜን
ልክ እንደ መብረቅ አሜን አሜን
ከላይ እያበራ አሜን አሜን
ዳግም ይመለሳል አሜን አሜን
ከቅዱሳን ጋራ አሜን አሜን
ስምን ያተረፉ በየዘመናቸው
ተከታዮቻቸው ሲሞቱ ረሷቸው
ሁለት ሺ ዓመት ታሪክ ያልሸፈነው
ሰንጥቆ የመጣ የኢየሱሴ ስም ነው
ይኼን ስሰማ አሜን በማለቴ
ሰመረ ብርሃን በራ ቤቴ
አሜን በማለቴ (3X)
ሰመረ ሂወቴ
አሜን ያልኩት ጌታ (3X)
እስራቴን ፈታ