አማላጄ (Amalaje) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(2)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

የኢየሱስ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው
የጌታዬ ደም ዛሬም ትኩስ ነው (2X) አማላጄ ነው

  የሰው ዘር ሁሉ ያዳም ስህተት
ይዞት ወደቀ ወደ ጥፋት (2X)

  ማንም እንዳይድን ይሄን ቢረዳ
ሊከፍለው መጣ ለኃጢያት ዕዳ አወይ ለእኔ ዕዳ
  የኃጢያት ደሞዝ ነውና ሞት

ሞቴን ሞተልኝ ሰጠኝ ሂወት (2X)
  ኃጢያት ተሻረ ከእኔ ላይ

በፈሰሰልኝ ጎልጎታ ላይ ቀራኒዮ ላይ
በገዛ ደሙ እርቅ አወረደ
የጠፋሁትን ስለወደደ
ኃጥዕ ተብዬ ስም ለወጣልኝ
በደሙ አንፅቶ ፃድቅ አስባለኝ
ከደጉ አባቴ አሁን ታረኩ
በቅዱስ ደሙ ስለታጠብኩ
ሌላ አማላጅ ሳያስፈልገኝ
በቀኙ ሆንኩ ደሙ አቀረበኝ
የኢየሱስ ደም.....
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ፀሎት ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላነፃኝ
የማን ፀሎት ነው የሚያነፃኝ
የኢየሱስ ደም ሳያስታርቀኝ
የማን ምልጃ ነው የሚያስታርቀኝ
የኢየሱስ ደም ያላጠበኝ

 የማን ምልጃ ነው የሚያጥበኝ
  ያስታረቀኝ ከአባቱ አማላጅ የሆነልኝ
  ስለ ኃጢያቴ ጥብቅና በአብ ፊት የቆመልኝ

የኢየሱስ ደም.....
ለሆንኩት ለኔ ለሞት ፍርደኛ
በአብ ቀኛ ያለው አንዱ ብቸኛ
ስለበደሌ እሱ ነው ዋሴ
የሚቆምልኝ ልክ እንደ ራሴ
መሰላል ያየው ያዕቆብ በህልሙ
መካከለኛ ነው ክቡር ደሙ
ሰማይ ከእኔ ጋር ዕርቅ ያደረገው
በማንም አይደል በኢየሱስ ደም ነው
ያስታረቀኝ ከአባቱ....