አለሁ (Alehu) - በረከት ተስፋዬ

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ
በረከት ተስፋዬ
(Bereket Tesfaye)

Lyrics.jpg


(3)

መምህሩ
(Memheru)

ዓ.ም. (Year): ፳ ፻ ፭ (2015/2023)
ቁጥር (Track):

(1)


ሌሎች ፡ የአልበሙ ፡ መዝሙሮች
(Other Songs in the Album)
የበረከት ተስፋዬ ፡ አልበሞች
(Albums by Bereket Tesfaye)

አለሁ በምህረቱ አለሁ በይቅርታው (እየማረኝ) አለሁ
አለሁ ምህረት አጊንቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ
አለሁ በምህረቱ አለሁ እየማረኝ አለሁ
አለሁ ምህረት አጊንቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ

  አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህረቱ ገኗል አለሁ
  አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ(2x)

እነ ሚካኤል እነ ገብርኤል
እነ ሱራፌል እነ ኪሩቤል
በክንፎቻቸው ተከልለውት
ፊቱ ሚቆሙለት አምላክ የሚሉት
በገራፊዎች ፊት ቆመልኝ እሱ ግን ስለ እኔ
ፍቅር ግድ ቢለው ሊያወጣኝ ከኃጢያት ከኩነኔ
ዙፋን የነበረው ከሰማይ ዳዊትን የረዳ
ተንከራተተልኝ ኢየሱስ ከናዝሬት ይሁዳ
ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ
እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንድ ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የእኔን ልብሰ ለበሰ
ቆሻሻ ሂወቴን በደሙ ቀደሰ

  አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህረቱ ገኗል አለሁ
  አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ(2x)

ይሁን በምትል ቃል ፍጥረትን የሰራ
ጥበብ የሻተውን ጥበብን ያስወራ
አባቶች ሲጠሩት በእሳት የመለሰ
እረኛው ዳዊትን ተናግሮ ያነገሰ
እንደሚታረድ በግ ዝም አለ ስለ እኔ ኢየሱስ
ፍቅርን የኖረ በተግባር የፍቅር ንጉስ
ምድርን ያቆመ በቃሉ ያላንዳች ምሶሶ
እሱ ግን ዝም አለ ሞተልኝ የእኔን ውርደት ለብሶ
ፍቅሩ ፈሰሰ ከምህረት ደጅ
እግዚአብሔር ከሰማይ ሰጠኝ አንዱን ልጅ
ኑሮዬን ኑር አለኝ የእኔን ልብስ ለበሰ
ቆሻሻ ህይወቴን በደሙ ቀደሰ

  አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህረቱ ገኗል አለሁ
  አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ(2x)

አለሁ በምህረቱ አለሁ በይቅርታው አለሁ
አለሁ ምህረት አጊንቻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ
አለሁ በምህረቱ አለሁ እየማረኝ አለሁ
አለሁ ፍቅሩን ቀምሻለሁ እኔ ምን እሆናለሁ

  አለሁ ሞቴ ተሽሯል አለሁ ምህረቱ ገኗል አለሁ
  አለሁ ህመሜን ወስዷል አለሁ እኔ ምን እሆናለሁ(2x)

አብ ከላይ ሆኖ ለኔ ራራልኝ አዘነ
ሊያድነኝ ሽቶ አንድ ልጁ ላይ ጨከነ
ፍቅር ልሂድ አለ ታዘዘ ለአባቱ
ክብሩን ትቶ ወርዶ አዳነኝ በሞቱ
ፍቅር እንደ ኢየሱስ የለም (8X)